(ዝነኞች በመሞቻቸው ሰዓት የተናገሩት)
· ‹‹የመጨረሻ ቃል የሚያስፈልገው በህይወት ሳሉ በቅጡ ሳይናገሩ ለቀሩ ጅሎች ነው፡፡››
ካርል ማርክስ (ፈላስፋ)
· ‹‹ከሸክላ የተገነባች ሮም አገኘሁ፤ እምነበረዷን ሮምን ትቼላችሁ እሄዳለሁ፡፡››
አጉስተስ ቄሳር
(የመጀመሪያው የሮማ ንጉስ፣ ለህዝቡ የተናገረው)
· ‹‹ለመሞት ቅንጣት ታህል አልፈራሁም።››
ቦብ ማርሊ (ሙዚቀኛ)
· ‹‹እግዚአብሔርንና የሰው ልጅን አስቀይሜአለሁ፤ ምክንያቱም ሥራዬ ሊኖረው የሚገባው የጥራት ደረጃ ላይ አልደረሰም››
ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ (ፈልሳፊና ሰዓሊ)
· ‹‹ዛሬ ማታ እሄዳለሁ››
ጄምስ ብራውን (ሙዚቀኛ)
· ‹‹ሁሉም ደስተኛ ነው? ሁሉም ሰው ደስተኛ እንዲሆን እሻለሁ፡፡ እኔ ደስተኛ መሆኔን አውቃለሁ››
ኢቴል ባሪሞር (ተዋናይት)
· ‹‹አሁን ልተኛ ነው፤ ደህና እደሩ››
ሎርድ ጆርጅ ባይሮን (ፀሐፊ)
· ‹‹መግባት አለብኝ፤ ጉሙ እየገለጠ ነው››
ኢሚሊ ዲክንሰን (ገጣሚ)
· ‹‹እዚያ በጣም ውብ ነው››
ቶማስ አልቫ ኤዲሰን (ፈልሳፊ)
· ‹‹አዎ ከባድ ነው፤ ኮሜዲ የመስራት ያህል ግን አይከብድም›› (መሞት ከባድ እንደሆነ ተጠይቆ የመለሰው)
ኢድመንድ ግዌን (ተዋናይ)
· ‹‹ጥቁር ብርሃን ይታየኛል››
ቪክቶር ሁጎ (ፀሐፊ)
· ‹‹ንግስት ነኝ፤ ነገር ግን ክንዶቼን የማንቀሳቀስ ሃይል የለኝም››
ሉይስ (የፐርሽያ ንግስት)
· ‹‹ምስኪን ነፍሴን ጌታ ይርዳት››
ኤደጋር አላን ፓ (ፀሐፊ)
· ‹‹ምንም ያልተበረዘ 18 መለኪያ ውስኪ ገልብጫለሁ፤ ይሄ አዲስ ክብረ ወሰን ይመስለኛል….››
ዳይላን ቶማስ (ገጣሚ)
Published in
የግጥም ጥግ