Print this page
Sunday, 25 December 2016 00:00

‹‹ኢትዮጵያዊያን ፈርዖኖች›› መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በአሜሪካዊቷ ዶ/ር ድሩሲላ ጁንዲ ሂውስተን ‹‹Wonderful Ethiopians of The Ancient Cushitic Empire›› በሚል ርዕስ ከረጅም አመታት በፊት የተፃፈውና በአንጋፋው ጋዜጠኛና ተርጓሚ ግርማዬ ከበደ ‹‹ኢትዮጵያዊያን ፈርዖኖች›› በሚል የተተረጎመው መፅሀፍ፤ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በዋናነት የሰባት ሺህ አመታት እድሜ ያለውን የኩሽና የአክሱም ስልጣኔ በማስረጃ እያስደገፈ ያብራራል፡፡
መምህር ጋዜጠኛና የታሪክ ተማራማሪ የሆነችው ዶ/ር ድሩሲላ ጁነዲ ሂውስተን፤ ይህንን ታሪክ ከሌሎች ደባልና የተቀላቀሉ ስልጣኔዎች ለይታ ጥርት ባለ መልኩ ለመፃፍና የኢትዮጵያንን ጥንት-ስልጣኔ መነሻና መድረሻ ለማወቅ የረጅም ጊዜ ምርምር እንዳደረገች ተርጓሚው በማስታወሻው አስፍሯል፡፡ በ240 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ81 ብር ከ50 ሳንቲም ለገበያ የቀረበ ሲሆን ዩኒቲ መፅኀፍት መደብር እያከፋፈለው ይገኛል፡፡

Read 1797 times