Saturday, 31 December 2016 11:52

“ኅብረ- ብዕር” ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

 በደራሲና ጋዜጠኛ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር የተዘጋጀው “ኅብረ- ብዕር” ሦስተኛ መጽሐፍ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ አዘጋጁ ካሁን ቀደም በተመሳሳይ ርዕስ ሁለት ቅጽ መጻሕፍት ያዘጋጁ ሲሆን 210 ገፆች ባሉት በአሁኑ መጽሐፍ ወጎች፣ ግጥሞች፣ ሽለላ፣ የቦታ ሥያሜዎችና ሌሎችም ተካትተዋል፡፡ በፋር ኢስት ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር የታተመው መጽሐፍ፤ በ69.60 ብር እየተሸጠ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ሬዲዮ የእሁድ ፕሮግራም፣ ወጎች በማቅረብ የሚታወቁት ደራሲ ጋዜጠኛና የወግ ጸሐፊ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር፤ ከ”ኅብረ-ብዕር” ቅጾች በተጨማሪ “ብፁአን እነማን ናቸው?”፣ “ምንኩስና በኢትዮጵያ” እና “ባህል እና ክርስትያናዊ ትውፊት በኢትዮጵያ” የተሰኙ በመረጃ የዳበሩ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አበርክተዋል፡፡ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሚታተመው “ዜና ቤተክርስትያን” ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ናቸው፡፡

Read 2372 times