Sunday, 08 January 2017 00:00

‹‹በፍቅር ስም›› መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

ለረጅም ዓመታት በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ማህበራዊና ጥበባዊ መጣጥፎችን በአምዳኝነት በማቅረብ የሚታወቀው ዝነኛው ደራሲና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ‹‹በፍቅር ስም›› የተሰኘ ልብወለድ መፅሀፍ ለንባብ አበቃ፡፡ ‹‹ዓለማየሁ ህይወትን ባልተለመደ በተገለለ የማህበረሰባችን አካል ዓይን እንድናይ ዕድል የሰጠን፣ ሌላኛው ድህረ ዘመናዊ ድርሰቱ ነው›› ብሏል የስነፅሁፍ ተመራማሪ ቴዎድሮስ አጥላው በመፅሃፉ ጀርባ በሰጠው አስተያየት፡፡ መፅሀፉ  በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ተከፋፍሎ በ216 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን በ71 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም ‹‹ቅበላ››፣ ‹‹የብርሀን ፈለግ››፣ ‹‹አጥቢያ››፣ ‹‹ኩርቢት›› እና ‹‹ወሪሳ›› የተሰኙ ተወዳጅ መፅሃፍትን ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡

Read 1509 times