Saturday, 14 January 2017 15:54

ሳምሰንግ በቀውስ ውስጥ ሆኖም ትርፉ በ50 በመቶ ጨምሯል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ድንገት በእሳት በሚጋየው ጋላክሲ ኖት 7 ምርቱ ሳቢያ በታሪኩ የከፋ በተባለው ቀውስ እየተናጠ አመቱን የሸኘው ግዙፉ ሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ፤ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም በመጨረሻው የሩብ አመት ትርፉ ካለፈው አመት በ50 በመቶ እድገት ማሳየቱን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው ባለፈው ሳምንት ይፋ ባደረገው መረጃ፣ የ2016 የመጨረሻው ሩብ አመት ትርፉ ባለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ካስመዘገበው ትርፍ የ50 በመቶ ያህል ጭማሪ በማሳየት፣ 7.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን እንዳስታወቀ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ሳምሰንግ በአመቱ ያስመዘገበው ገቢ ካለፈው አመት የ10 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንና ይህም ባለፉት ሶስት አመታት ካገኘው ገቢ ከፍተኛው መሆኑን የጠቆመው ዘገባው፤ ትርፋማነቱ ማደጉን ይፋ ማድረጉን ተከትሎም የአክሲዮን ድርሻው በ1.9 በመቶ ማደጉን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው ከገባበት ቀውስ ለመውጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ያመለከተው ዘገባው፤ የተለያዩ ምርቶቹን በስፋት ወደ ገበያ ለማቅረብ በማቀድ በአስር ቢሊዮኖች ዶላር መድቦ፣ የማስፋፊያ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጧል፡፡

Read 1090 times