Saturday, 14 January 2017 16:01

2ኛው ‹‹ህብረትርኢት›› ግጥም በጃዝ ተካሄደ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ማይና ኢንተርቴመንት ከኢትዮጵያ ሆቴል ጋር በመተባበር ሁለተኛውን ‹ህብረ ትርኢት›› የግጥም በጃዝ ምሽት ትላንት ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ
በኢትዮጵያ ሆቴል አቀረቡ፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ግጥም በጃዝ፣ ስታንዳፕ ኮሜዲ፣ አጭር ተውኔት፣ ወግና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ስራዎች ለታዳሚው ቀርበዋል፡፡አርቲስት ቅድስት ብሩክ፣ ካሌብ ዋለልኝ፣ እታፈራሁ መብራቱ፣ ዮናስ ጌታቸው እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን በየፕሮግራሙ የሚቀርበውን አጭር ተውኔት በድርሰትና በትርጉም ፍቅሩ ካሳ፡፡ በዝግጅት ማህሌት ሰለሞን ይሰሩታል ተብሏል፡፡ ወር በገባ በመጀመሪያው አርብ በተከታታይ ይካሄዳል በተባለው የኪነ-ጥበብ ምሽት ላይ ለመታደም የመግቢያ ዋጋ አንድ መቶ ብር እንደሚከፈል ለማወቅ ትችሏል፡፡

Read 2105 times