Saturday, 14 January 2017 16:03

‹‹አዲስ አምቡጦች›› የድምፅ ውድደር ዛሬ ይጠናቀቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

በ96.3 ኤፍ ኤም የሚተላለፈው አቢሲኒያ ኢንተርቴይመንት 6ኛው ‹‹አዲስ አምቡጦች››
የቀጥታ የሬዲዮ የድምፅ ውድድር ዛሬ ይጠናቀቃል። ለመጨረሻው ዙር ያለፉት አምስቱ ተወዳዳሪዎች ተለይተው መታወቃቸውን የፕሮግራሙ አዘጋጅ አንጋፋው ጋዜጠኛ አባተ ማንደፍሮ ገልጿል፡፡ አቢሲኒያ ኢንተርቴይመንት መተላለፍ የጀመረበትን 6ኛ አመትም በዛሬው ዕለት እንደሚያከብር ታውቋል፡፡ ለመጨረሻው ዙር ካለፉት 5ቱ ጀማሪ ድምፃዊያን መካከል ከ1-3 ለወጡት አሸናፊዎች የሬዲዮ ፕሮግራሙ ከግጥምና ዜማ ደራሲዎችና አቀናባሪዎች ጋር በመተባበር ለእያንዳንዳቸው ነጠላ ዜማ ያሰራላቸዋል ተብሏል፡፡ ላለፉት አምስት አመታት በየዓመቱ ተመሳሳይ ውድድር ሲካሄድ የቆየ ሲሆን እስካሁን ከ20 በላይ አሸናፊዎች የእድሉ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ጋዜጠኛ አባተ ጨምሮ ገልጿል፡፡ አቢሲኒያ ኢንተርቴይመንት የመዝናኛና የቁምነገር ፕሮግራም ሲሆን በቀጥታ የሬድዮ ስርጭት ድምፃዊያንን የሚያወዳድር ብቸኛ የሬዲዮ ፕሮግራም መሆኑ ተገልጿል፡፡

Read 1735 times