Saturday, 14 January 2017 16:03

የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የቋንቋና ባህል ምርምር ኮንፈረንስ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(8 votes)

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ይካሄዳል
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያውን ሀገር አቀፍ የቋንቋና ባህል ልማት የምርምር ኮንፈረንስ ዛሬና ነገ ያካሂዳል፡፡በአማርኛ ቋንቋዎች የትምህርት አሰታጥ ችግሮች ላይ ቀደም ሲል ጉባኤና የተደረገ ሲሆን በጉባኤው
የአማርኛ ብቻ ሳይሆን በቀድሞ ወሎ ጠቅላይ ግዛት ስር ይኖሩ የነበሩ እንደ ግዕዝና ኦሮሚኛ ቋንቋዎች ላይ ምርምር ለማድረግ ክበባት መደራጀታቸውን ተከትሎ፣ ይህ ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ ሊቋ ቋም መቻሉን አቶ ሰይድ ይማም፣ በወሎ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ስነ -
ፅሁፍ ት/ት ክፍ፤ የአማርኛ ተጠሪ ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በአገር አቀፍ የምርምር ኮንፈረንሱ ላይ የግዕዝ፣ የአማርኛና ኦሮሚኛ ቋንቋዎች ስርአተ ፅህፈት፣ የአማርኛ ቋንቋ ሞክሼ ሆሄያት የወደፊት እጣፈንታ፣ የየቋንቋዎቹ ሰዋሰዋዊ ባህሪያት፣ የየቋንቋዎቹ ታሪካዊ እድገት፣
ቋንቋና ትምህርት፣ ከልማት አንፃር፣ ቋንቋና ባህል፣ቋንቋና ስርአተ ፆታ፣ በአማርኛ ቋንቋ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ጣልቃ ገብነት … ላይ የምርምር ፅሁፎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ የምርምር ፅሁፎቹን 15 የቋንቋ ስነ ፅሁፍ ምሁራን እንደሚያቀርቡ ለማወቅ ተችሏል።በወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚካሄደው ጉባኤ፤ የመጀመሪያው ሲሆን በቀጣይ ተከታታይነት እንዲኖረው ይደረጋል ብለዋል፤ አቶ ሰይድ፡፡

Read 4681 times