Wednesday, 25 January 2017 07:21

ባለ አራት ኮከቡ አዜማን ሆቴል ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 ከወራት በፊት ስራ የጀመረውና ከአትላስ ሆቴል አለፍ ብሎ የሚገኘው ባለ አራት ኮከቡ አዜማን ሆቴል፤ ዛሬ ረፋድ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ አስጎብኚ ድርጅቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል፡፡
በኢትዮጵያዊ ባለሀብት የተሰራው ሆቴሉ፤79 የመኝታ ክፍሎች፣ ከ300 በላይ ሰዎችን የሚይዝ አዳራሽ፣ እያንዳንዳቸው 70 ሰዎች የሚይዙ ሌሎች ሁለት አዳራሾች፣ ባርና ሬስቶራንት፣ ደረጃውን የጠበቀ የወንዶችና ሴቶች ስፓ፣ በቂ የመኪና ማቆሚያና መሰል አገልግሎቶችን ያሟላ ነው ተብሏል፡፡ ሆቴሉ ሥራ በጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ እውቅናን በማግኘቱ  ስብሰባዎችን፣ ሰርጎችንና ሌሎች ትልልቅ ሁነቶችን እየተቀበለና በበቂ ባለሙያዎች እየታገዘ በማስተናገድ ላይ ነው ያሉት የሆቴሉ ኃላፊዎች፤ ለ120 ሰራተኞች የስራ እድል መፍጠሩንም ገልጸዋል፡፡  

Read 1263 times