Wednesday, 25 January 2017 07:28

ጃፓን ዜጎቿ ስራ እንዳያበዙ ልታግድ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

   20 በመቶ ጃፓናውያን ሰራተኞች ለሞት የሚያሰጋ ስራ ይሰራሉ

       የጃፓን መንግስት ዜጎቹ ከሚገባው በላይ ስራ በመስራት ለአደጋ እንዳይጋለጡ ለማድረግ በማሰብ፣ የትርፍ ስራ ሰዓት ገደብ የሚጥል ህግ ሊያወጣ ማቀዱን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘገበ፡፡
በርካታ የአገሪቱ ዜጎች ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት በማሰብ፣ ከመደበኛው የስራ ሰዓታቸው በተጨማሪ የትርፍ ጊዜ ስራ በመስራት ብዙ ሰዓት ተጠምደው እንደሚውሉና እንደሚያድሩ የጠቆመው ዘገባው፤ከዚህ ጋር በተያያዘ ብዙዎች ለጤና ችግር ብሎም ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ መንግስትን እንዳሳሰበው ገልጧል፡፡
20 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ሰራተኛ ህዝብ ከሚገባው በላይ ስራ በመስራት ለሞት የመጋለጥ አደጋ አንዣቦበታል ያለው ዘገባው፤ አብዛኞቹም በወር ከ80 ሰዓታት በላይ የትርፍ ጊዜ ስራ እንደሚሰሩ ገልጧል፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት በሚልም የአገሪቱ መንግስት ከመጪው ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የትርፍ ሰዓት የስራ ገደብ የሚያስቀምጥ ህግ ለማውጣት መወሰኑን ዘገባው አስረድቷል፡፡

Read 1119 times