Wednesday, 25 January 2017 07:27

ትልቁ ጆርጅ ቡሽ ሆስፒታል ገብተዋል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  የ92 አመቱ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤች ደብሊው ቡሽ ባጋጠማቸው የጤና እክል የህክምና እርዳታ ለማግኘት ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ጀምሮ ሂዩስተን በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ቡሽ ከዚህ ቀደምም ለሁለት ጊዚያት ወደዚህ ሆስፒታል ገብተው የመተንፈሻ አካላት ህክምና እንደተደረገላቸው ያስታወሰው ዘገባው፣ በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና ከቀናት በኋላ ህክምናቸውን ጨርሰው ይወጣሉ ተብሎ ከመጠበቁ ውጪ ወደ ሆስፒታል ያስገባቸው በሽታ ምን እንደሆነ አለመገለጹን አስረድቷል፡፡
አሜሪካን እ.ኤአ. ከ1989 እስከ 1993 ያስተዳደሩት 41ኛው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤች ደብሊው ቡሽ፣ በፓርኪንሰንስ ህመም ሳቢያ ራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ አቅቷቸው፣ በሰው ድጋፍና በተሽከርካሪ ወንበር ታግዘው መንቀሳቀስ ከጀመሩ አመታት እንዳለፏቸውም ዘገባው አብራርቷል፡፡
ቡሽ ትናንት በተካሄደው የዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ቀጠሮ ቢይዙም ሆስፒታል በመግባታቸው ሳቢያ በዝግጅቱ ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ተነግሯል፡፡

Read 1577 times