Wednesday, 25 January 2017 07:35

ባለፈው ዓመት በአማካይ በየአራት ቀኑ አንድ ጋዜጠኛ ተገድሏል

Written by 
Rate this item
(3 votes)

  በተጠናቀቀው የፈረንጆች አመት 2016፣ በአለማችን የተለያዩ አገራት ከ100 በላይ ጋዜጠኞች መገደላቸውን ያስታወቀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፤ በአመቱ በአማካይ በየአራት ቀኑ አንድ ጋዜጠኛ መገደሉን ገለጸ፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም( ዩኔስኮ) በአለማቀፍ ደረጃ የተሰራን የጥናት ውጤት ጠቅሶ እንዳለው፣ በአመቱ በርካታ ጋዜጠኞች የተገደሉት በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአረብ አገራት ሲሆን በርካታ ግድያዎች የተፈጸሙት በሶርያ፣ ኢራቅና የመን ነው፡፡ ምንም እንኳን የጋዜጠኞች ግድያ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ዘንድሮ ቢቀንስም፣ በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው የመብት ጥሰትና ግድያ በአለማቀፍ ደረጃ እየተባባሰ ነው ያለው ተቋሙ፤ መንግስታት የጋዜጠኞችን ግድያዎች እንዲያጣሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በፈረንጆች አመት 2015 በአለማችን የተለያዩ አገራት ስራቸውን በማከናወን ላይ ሳሉ የተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር 115 እንደነበርም ተቋሙ አስታውሷል፡፡

Read 2055 times