Monday, 30 January 2017 00:00

በዛምቢያ ታስረው የነበሩ 147 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተመለሱ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

የዛምቢያ መንግስት በህገወጥ መንገድ ወደ ግዛቴ ገብተዋል በሚል አስሯቸው የነበሩና በቅርቡ ይቅርታ ያደረገላቸውን 147 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከትናንት በስቲያ ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቋል፡፡
እነዚሁ 145 ወንድ እና 2 ሴት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት ድጋፍ ባለፈው ሃሙስ ተሲያት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን፣ የአገሪቱ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ማስታወቁን ዥንዋ ትናንት ዘግቧል፡፡

Read 2587 times