Print this page
Saturday, 28 January 2017 11:44

“ደም ልገሳ በኢትዮጵያ - ከ1962 ዓ/ም ጀምሮ”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

 • ደም መስጠትም ሆነ መቀበል ሰጪውንም ሆነ ተቀባዩን የማይጎዳ ሰብአዊ አገልግሎት ነው።
        • ደም መለገስ ማለት ልትቋረጥ የነበረችን ሕይወት እንደገና ተስፋዋን ማለምለም የሆነ ሰብአዊ አገልግሎት ነው።
        • ደም በፈቃደኝነት መለገስ... የስጦታዎች ሁሉ ስጦታ ነው።

                                        “ደም ልገሳ በኢትዮጵያ - ከ1962 ዓ/ም ጀምሮ”

     ደም መስጠትም ሆነ መቀበል ሰጪውንም ሆነ ተቀባዩን የማይጎዳ ሰብአዊ አገልግሎት ነው።
ደም መለገስ ማለት ልትቋረጥ የነበረችን ሕይወት እንደገና ተስፋዋን ማለምለም የሆነ ሰብአዊ አገልግሎት ነው።
ደም በፈቃደኝነት መለገስ... የስጦታዎች ሁሉ ስጦታ ነው።
መርሐ ቤተ አለምከተማ ሜንሽን ፎር ሜንሽን ያሰራው ሆስፒታል ለስራ በተንቀሳቀስንበት ማለትም ከሶስት አመት በፊት ያጋጠመን ታሪክ እንደሚከተለው ነበር።
“አንዲት እናት በምጥ ተይዛ ወደሆስፒታሉ በባህላዊው ቃሬዛ በሸክም ትደርሳለች። የመጣችው ራቅ ካለና አቀበትና ቁልቁለት ከበዛበት አካባቢ በመሆኑ ለእርዳታ ማለትም ለሸክሙ ለመተጋገዝ አብረው የመጡ ብዙ ገበሬዎች ናቸው። ሌሎች የቤተሰቡ አባላትም አብረው አሉ። እናትየውን ልጅዋን ከተገላገለች በሁዋላ ብዙ ደም መፍሰስ ይጀምራል። ሐኪሞቹም ሴትየዋን ይዘው ከመ ጡት ቤተሰቦች መካከል አንድ ሁለት ሰዎች ደም ቢሰጡ ጥሩ ነው አሉና ሁኔታው ተነገራ ቸው። በቅድሚያ ባልተቤትዋ ነበር መልስ የሰጠው።
“...አ...አ...ይ... እኔማ በዚህ ላይ ገበሬ ነኝ። እንደገና ደግሞ ከቤት ልጆች አሉ። እኔ ደም ሰጥቼ ታዲያ እነርሱን ማን ሊያሳድግ ነው? አለ።
ሌሎቹም በየፊናቸው መልስ ሰጡ።
“እኔ ለራሴም ጤና የለኝ...እኔም ለራሴ አጥን ወጥቶ... ከምኔ ላይ ነው ደም የሚቀዳ...አጀብ...”
“አረ እኔ ለራሴ አርጅቻለሁ...ለመሆኑ ደም ቢፈለግስ ይገኛል?”... ሌላም ሌላም መልሶች ተሰጡ።
ከዚያም በንዴት በፍጥነት ሐኪሞቹ ተነጋገሩና አምሳያ ደም ያላቸው ተመርምረው ሰጡአት። ሴትየይቱን እንደምንም ወደጤናዋ ከመለስን በሁዋላ... እንደገና ተመካከርን። አንዱን ባለሙያ... ሂድና... ሞታለችና እሬሳ ለመቀበል ተዘጋጁ በላቸው ...አልነው። እሱም ልክ እንደተነገረው ሄደና ነገራቸው። ከዚያም ፡-
ሆስፒታሉ በር ላይ እየተቀባበሉ ኡኡታቸውን አቀለጡት። እየተንጎራደዱ... ኩታቸውን ወገባቸው ላይ እየታጠቁ... ጭንቅላታቸውን ይዘው ከወዲያ ወዲህ እያሉ ልቅሶውን አቀለጡት። ትንሽ ከተላቀሱ በሁዋላ ሌላው ሐኪም ደግሞ ወጣና “አረ... ይበቃችሁዋል። በቃ አታልቅሱ። ሴትየይቱ ሐኪሞቹ ደማቸውን ሰጥተዋት አድነዋታል” አላቸው። ከዚያም እርስበርሳቸው ተያዩና፣ “አረግ...አረግ... እንዴት ተደርጎ”... መባባል ሲጀምሩ። ደም የሰጡ ሰዎች በግንባር ቀርበው ሁኔታውን አስረዱዋቸው። እናም ደም መስጠት በጎ ተግባር መሆኑን... ሰጪውንም እንደማይጎዳ ሲያስረዱዋቸው። “እንዲህማ ከሆነ እኛም እንሰጣለን” ብለው በጊዜው ደም ከመስጠት ባሻገርም፣ ዛሬም ድረስ የፈቃደኝነት ደም ለጋሾች ሆነው ቀናቸውን ጠብቀው ጊዜው ሲደርስ እየመጡ ደም ይለግሳሉ። “እራሳቸው ብቻም ሳይሆኑ በአካባቢያቸው የተፈጠረውን ነገር በማስረዳት ሌሎችንም አስተባብረው ዛሬ በሆስፒታሉ የደም ችግር የለም” የሚል ነበር በጊዜው የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አየለ ተሾመ ለአምዱ አዘጋጅ የሰጡት ትውስታ።
በዚህ እትም ስለደም ልገሳ የሚያወጉን አቶ ሚኪያስ ማሞ በብሄራዊው የደም ባንክ የክሊኒክ አስተባባሪ ናቸው። እሳቸውም እንዳሉት “..ደም ልገሳ ሲባል እራሱ መስፈርት አለው። ማን ይለግሳል? ለማን ይለገሳል? እንዴት ይለገሳል? የሚል የራሱ ደረጃ ያለው ሰብአዊ አገልግሎት ነው። የደም ባንክ አገልግሎት በአገራችን የተጀመረው በ1962 ዓ/ም ሲሆን ታሪካዊ አጀማመሩም ብዙ ውጣ ውረዶች የነበረበት ነው። አቶ ሚኪያስ በ1962 ዓ/ም የነበረውን ልምድ ሲገልጹ ፡-
“ማህረሰቡ ባለው የግንዛቤ ደረጃ ከጊዜ ወደጊዜ እየተለወጠ በመምጣቱ ዛሬ በፈቃደኝነት ደም የመለገስ አስተዋጽኦ እያደረገ ቢሆንም ደም መስጠት በተጀመረበት ዘመን ግን ተግባሩን ለማስ ለመድ ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች እንደነበሩ አይካድም። ቀደም ባለው አሰራርም የነበረው የምትክ ደም አሰባሰብ ተግባር ዛሬ እንዲቅር የመሆኑም እውነታ ሰዎች በፈቃደኝነት ደም መስጠትን እንዲለምዱት በመደረጉ ነው። ስለሆነም አሁን ማንኛውም ሕመምተኛ ደም ቢያስ ፈልገው እንደቀድሞው ከዘመድ አዝማድ በማሰባሰብ ሳይሆን ባንኩ አስቀድሞውኑ ባሰባሰበው ደም እንዲ ጠቀሙ ማድረግ ተችሎአል።”ብለዋል።
አቶ ሚኪያስ በማከልም፣ “የዛሬ 47 አመት ደም ልገሳ በኢትዮጵያ ሲጀመር አንዳንድ ሀሳቡን በበጎ የተቀበሉና እውቀቱ የነበራቸው ሰዎች የመኖራቸውን ያህል ድርጊቱን እንደሰይጣን ድርጊት የሚመለከቱት እንደነበሩ ይታወቃል። ከጊዜ ወደጊዜ ግን ስልጣኔው እየጨመረ የሌላው አለም ተሞክሮ እየታየ የደም ልገሳ ሰብአዊ አገልግሎት መሆኑ ታምኖበት እነሆ ዛሬ በቂ ባይ ባልም የተሻለ ደረጃ ላይ ተደርሶአል። በቀድሞው ጊዜ ቤተሰብ ታምሞ እንኩዋን ደም ለግሱ ሲባሉ እንቢ የሚሉ ሰዎች ቢኖሩም ዛሬ ግን ከተሸለ ግንዛቤ ላይ በመደረሱ ሰዎች ለማያው ቋቸው ሰዎች ሕይወት ለማዳን ደም በፈቃደኝነት ከመለገስ ደረጃ ተደርሶአል።”
በአለም የጤና ድርጅት መስፈርት መሰረት አንድ ሐገር ባላት የሕዝብ ብዛት መጠን 1% ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ሊኖራት ይገባል። ከዚህ ስንነሳ በኢትዮጵያ ወደ 90 ሚሊዮን ሕዝብ አለ ቢባል 900 ሺህ የሚደርሱ የበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች ሊኖሩ ይገባል። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በኢትዮ ጵያ ያሉት የፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር ከ140-160ሺህ የሚደርስ ነው። ይህ ቁጥር ከሚፈለገ ው ቁጥር ከእሩብ በታች መሆኑ እርግጥ ነው። ይህ ከነበረው የተሻለ ቢሆንም አሁንም ግን ይህንን ሰብአዊ አገልግሎት ለማስተዋወቅ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ እሙን ነው። ደም መስጠትም ሆነ መቀበል ሰጪውንም ሆነ ተቀባዩን የማይጎዳ ሰብአዊ አገልግሎት ነው። ደም የመቀበልና የመስጠት ተግባር አሁን ባለበት ደረጃ በደም ባንክ ብቻ የሚሰራ ስራ ነው። አሁን ባለው ሂደት በተወሰኑ የመስተዳድር አካላት የደም ባንኮች ተቋቁመዋል። ለምሳሌም በትግራይ ክልል አክሱምና መቀሌ ላይ ሁለት የደም ባንኮች አሉ። በዚህ ሁኔታ ብሔራዊ የደም ባንኩን ጨምሮ ወደ 25 የሚደርሱ የደም ባንኮች በተለያዩ መስተዳድሮች ተቋቁመዋል። ስለዚህም በሙሉ በሐገሪቱ ያሉ የጤና ተቋማት አገልግሎቱን የሚያገኙበት የደም ባንክ ተለይቶ የተሰ ጣቸው በመሆኑ ከእነዚህ የደም ባንኮች ጋር ትስስር አላቸው። በእርግጥ የደም ክምችቱ በብሔ ራዊ ባንክ በዛ ያለ እና ሌሎች ጋ ግን አነስ ብሎ ከታየም የማስተላለፍ ስራ ይሰራል። አንዳንድ ጊዜ ግን እጥረት የሚያጋጥማቸው የደም አይነቶች ለምሳሌም -ሑ- የመሳሰሉ አር ኤች ኔጌቲቭ የሆኑ ደሞች እንደልብ ስለማይገኙ ምናልባትም የዛን አይነት ደም ያላቸው ሰዎች ደም እንዲሰጡ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈለጋል። ከዚያ ውጭ ግን ማንኛውም ሰው በፈቃደኝነት የሚለ ግሰው ደም ለሕመምተኛው እንደአግባቡ ይሰጣል።
ደም መለገስ ማለት ልትቋረጥ የነበረችን ሕይወት እንደገና ተስፋዋን ማለምለም የሆነ ሰብአዊ አገልግሎት ነው። ይህ ተግባር ከምንም በላይ የስጦታዎች ሁሉ ስጦታ ነው። ደም ለጋሹ ኪሎው ከ45 ኪሎ በላይ ሲሆን ጤናማ ሲሆን ረዥም ጊዜ ከሚቆዩ ጠንቀኛ ህመሞች ነጻ ሲሆን የሚሰጠው ደም ለታካሚው ሊደርስ የሚችል ሲሆን ነው ደም የሚለግሰው። የሚደረግለት የጤና ምርመራም የደም ግፊት፣ በሰውነት ውስጥ ያለው የደም መጠን... ወዘተ ተረጋግጦ ለጋሹም እንዳይጎዳ ተቀባይም እንዳይጎዳ በቂ ምርመራ ተደርጎ ነው ደም የሚሰጠው። ስለዚህም የሰውን ሕይወት ከማዳን የበለጠ ደስታን የሚፈጥር ነገር ስለሌለ ሰጪውም ሰው በማዳኑ ተቀባ ዩም ሕይወቱ በመትረፍዋ የሚደሰቱበት ነው። ከዚህም በላይ የጉበት በሽታ ቢ እና ሲ፣ ኤች አይቪ እና የቂጥኝ በሽታ በደም የሚተላለፉ በሽታዎች በመሆናቸው ደም በየሆስፒታሉ ከመሰራ ጨቱ በፊት እጅግ ዘመናዊ በሆኑ መሳሪያዎች ተመርምሮ እንዲወገድ ይደረጋል። ደም ለጋ ሹም እነዚህ ሕመሞች መኖር አለመኖራቸውን በነጻ በሚደረግለት ምርመራ እንዲያውቅ ስለሚ ደረግ ወደ ደም ባንክ በመምጣቱ ይጠቀማል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በባህሪው ንፉግ አይደለም። ደም መስጠትን በተመለከተ ስጋትና ፍርሐት ስለሚያድርበት እንጂ ሰውን ለማዳን ተሳትፎ ላለማድረግ ብሎ አይደለም። ስለዚህም በፈቃደኝነት ደም መለገስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በስፋት ማስተማር ፣ የግንዛቤ ለውጥ ማምጣት እና ህብረተሰቡን ወደተግባሩ ማምጣት የሚመለከታቸው ጠንክረው ሊሰሩበት የሚገባ ነው። ደም መለገስ ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ሕይወት የምንታደግበት ትልቅ ተግባር ነው። ስለዚህም ለወደፊቱ፡-
ደም ልገሳ የተከበረ እና ሰብአዊ ተግባር መሆኑን ለሕብረተሰቡ ተደራሽ በሆነ መልኩ በመገናኛ ብዙሀን በስፋትና በጥልቀት፣ በተከታታይነት መልእክቶችን ማስተላለፍ፡-
በዘመቻ መልክ በሚሰሩ ስራዎች አንድ ጊዜ የፈቃደኛ ደም ለጋሽ ሆኖ የሚቀረውን ሰው በዘለቄታዊነት እና በቋሚነት ደም በፈቃደኝነት እንዲለግሱ የማስቻል ስራ ያስፈልጋል። በዚህም አሰራሩ ከተጠናከረ ለምሳሌ... በኢትዮጵያ ወደ 900 ሺህ ያህል ደም ለጋሾች ያስፈልጋሉ ሲባል... ወደ 300 ሺህ ያህል ለጋሾች ቢኖሩና እነርሱ በቋሚነት በአመት ወደ 3 ጊዜ እያንዳንዳቸው ደም ቢለግሱ ከበቂ በላይ ደም ይገኛል ማለት ነው።
በክልል መስተዳድሮች ያሉ የደም ባንኮችን በማስፋት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ በወደፊት የአሰራር እቅድ በብሔራዊው የደም ባንክ ከተያዙት መንከል ናቸው።
 ማንም ሰው በተለይም እናቶች በደም እጦት ምክንያት መሞት የለባቸውም።

Read 5814 times