Saturday, 17 March 2012 10:08

የአድዋ ድል በኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ይዘከራል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ኬር ማስታወቂያ እና ፕሮሞሽን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ጋር በመተባበር የአድዋ ድልን 116ኛ ዓመት በተለያዩ ኪነጥበባዊ ዝግጅት እንደሚያከብር አስታወቀ፡፡ ከነገ ወዲያ ከቀኑ 11 ሰዓት በትያትር ቤቱ በሚቀርበው ዝግጅት ግጥም፣ ሽለላ፣ ፉከራ፣ ቀረርቶ፣ ትያትር፣ ውዝዋዜ፣ ሥዕል፣ ፎቶግራፍ እና ፊልም በዝግጅቱ ይቀርባል፡፡ ለዝግጅቱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የኪነጥበብ እና የመገናኛ ብዙሃን በተጨማሪነት እንዳገዙት ኬር ገልጿል፡፡

 

 

Read 1080 times Last modified on Saturday, 17 March 2012 10:10