Monday, 30 January 2017 00:00

“Intimate Red” የሥዕል ኤግዚቢሽን ዛሬ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ከቀይ ቀለም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላት በምትገልፀው ሰዓሊ ገነት ዓለሙ፤ የተሳሉ የሥዕል ስራዎች የሚቀርቡበት “Intimate Red” የተሰኘ የሥዕል አውደ ርዕይ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ ቀበና አካባቢ በሚገኘው አስኒ አርት ጋለሪ ይከፈታል፡፡ “ቀይ ቀለም ስለኔ መኖር፣ ስለ ሴትነቴና ስለመስዋዕትነት” እንዳስብ ያደርገኛል የምትለ ሰዓሊ ገነት፤ እነዚህን አስተሳሰቦቿን ለመግለፅ የሞከረችበት የሥዕል ስራዎቿ፤ ለ10 ቀናት ለዕይታ ክፍት ሆነው የሚቆዩ ሲሆን ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 4፡00 እስከ ምሽት 1፡00 ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 563 times