Monday, 30 January 2017 00:00

“የሀገሬ ንቅሳት” የግጥም መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(5 votes)


        በገጣሚ ሙሉዓለም ተገኘወርቅ የተፃፉ ከ30 በላይ ግጥሞችን የያዘውና በአገር ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥነው “የሀገሬ ንቅሳት” የተሰኘ የግጥም መድበል ሰሞኑን ገበያ ላይ ዋለ፡፡
ገጣሚው ከዚህ ቀደም በሲዲ ለአድማጭ ያደረሳቸውን 19 ያህል ግጥሞች በዚህ መፅሀፍ ውስጥ ማካተቱን ገልፆ፤ ግጥሞቹ በሲዲ ተወስነው እንዳይቀሩና ለአንባቢያን እንዲደርሱ መሆኑን በመግቢያው ላይ ገልጿል፡፡ በ119 ገፅ የተመጠነው መፅሀፉ፤ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 2152 times