Monday, 30 January 2017 00:00

“ነፃና ንፁህ” የሥዕል ትርኢት ትናንት ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ጋለሪያ ቶሞካ ለ22ኛ ጊዜ በሚያካሂደው የስዕል ትርኢት፤ “ነፃና ንፁህ” በሚል ርዕስ የሰዓሊ ይስሃቅ ሳህሌን የሥዕል ስራዎች ለእይታ አቀረበ፡፡ የሥዕል ትርኢቱ በትናንትናው እለት የተከፈተ ሲሆን የህፃናትን አለምና ህይወት የሚገልፁ የተለያዩ ስዕሎች የተካተቱበት ነው ተብሏል፡፡ “እንደ ህፃናቱ አሳሳል በወፍራም መስመራት የተሰመሩ፤ በሰፋፊ ዝርግና ደማቅ ህብረ ቀለማት የተቀቡ ነፃ፣ ንፁህና የዋህ ኪነ ቅቦች ናቸው” ብለዋል ሰዓሊ እሸቱ ጥሩነህ፤ ስለ ሰዓሊው ሥራዎች ባሰፈሩት አስተያየት፡፡ “ነፃና ንፁህ” የሥዕል ትርኢት ትናንት ተከፈተ ቀለማትን ማጫወት ደስ ይለኛል” የሚለው ሰአሊው፤ ከልጅነቱ ጀምሮ በኪነ ሥዕል ሙያ ራሱን ያዳበረ መሆኑ በሥዕል ትርኢቱ መግለጫ መፅሄት ላይ ተጠቁሟል። ሰዓሊው ከዚህ ቀደም በፈረንሳይ የባህል ማዕከል፣ በብሄራዊ ሙዚየም፣ በብሄራዊ ቴአትርና በአስኒ ቤተ ሥዕል ስራዎቹን ለዕይታ ማቅረቡ ታውቋል፡፡ “ነፃና ንፁህ”፤ ለሁለት ወራት ለተመልካች ክፍት ሆኖ
ይቆያል ተብሏል፡፡ ጋለሪያ ቶሞካ የሚገኘው ሳር ቤት ካናዳ ኤምባሲ ፊት ለፊት ነው፡፡

Read 1697 times