Sunday, 05 February 2017 00:00

‹‹ኔክስት ስቴጅ ፋውንዴሽን›› ለሜጄር ጀነራል ሀየሎም ት/ቤት ድጋፍ መስጠት ጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

     እ.ኤ.አ በ2015 የተቋቋመው ‹‹ኔክስት ስቴጅ ፋውንዴሽን›› ለሜጀር ጀነራል ሀየሎም አርአያ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ድጋፍ ማድረግ ጀመረ፡፡ ፋውንዴሽኑ በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኙ 50 ተማሪዎችን ቁርስና ምሳ በማብላትና የደንብ ልብስና የትምህርት ቁሳቁሶችን በማቅረብ ድጋፍ እንደሚያደርግ የፋውንዴሽኑ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ኤርሚያስ ጎርሜሳ ተናግረዋል፡፡
ተመሳሳይ ችግር ያለባቸውን በሌሎች ት/ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎችንም ለመደገፍ ጥናት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ ፋውንዴሽኑ ለተማሪዎች ከሚያደርገው ድጋፍ  በተጨማሪ የተማሪዎቹ ወላጆች በሆቴል መስተንግዶ፣ በምግብ ዝግጅትና በመሰል ስራዎች ስልጥነው ራሳቸውንና ልጆቻቸውን በተሻለ ሁኔታ ለማስተዳደር የሚያስችላቸው ስራ ለመስራት ዝግጅት መጀመሩን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በ2000 ዓ.ም የተመሰረተው የሜ/ጀ ሀየሎም አርአያ ት/ቤት ስራውን ሲጀምር በድንጋይ መቀመጫ ላይ ተማሪዎችን በመመዝገብ ነበር ያሉት የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ባደረገው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ለጋሾችን በመሰብሰብና ስለ ትምህርት ቤቱ ገለጻ በመስጠት መሠረታዊ ችግር ያለባቸው  ተማሪዎች የምግብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያገኙ ከማስቻል በተጨማሪ የቤተ መፅሀፍት የመማሪያ ክፍሎች እና ሌሎች መሰል ነገሮች እንደሟሉለት መደረጉን በት/ቤቱ የወላጆች ተማሪና መምህር ህብረት ሰብሳቢ አቶ ኤልያስ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ ት/ቤቱ በአሁኑ ሰዓት 769 ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተምር ተገልጿል፡፡

Read 1590 times