Sunday, 05 February 2017 00:00

የ‹‹ሰማያዊ›› የም/ቤት ሰብሳቢ፣ ህዝብን በማነሳሳት ተከሰሱ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(3 votes)

 የ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ብሄራዊ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸው ከበደ፣ የሀሳብ ወሬዎችን በማውራት፣ ሕዝብን በማነሳሳት ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን ከፍ/ቤት በዋስ ተለቀዋል፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከትናንት በስቲያ ክሳቸው የተነበበው አቶ ይድነቃቸው፤ ጳጉሜ 13 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከቀኑ በ3 ሰዓት፣ በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 9፣ ልዩ ቦታው ቂሎንጦ ማረሚያ ቤት አካባቢ፣ የህግ ታራሚ ቤተሰቦችን መንግስት ታራሚዎችን አቃጥሎ ለምን ዝም ብላችሁ ታያላችሁ? አትጮሁም ወይ፤ አታለቅሱም ወይ?! አሁን እኛም መታገል አለብን›› በማለት የቀሰቀሰ በመሆኑ በፈፀመው የሀሰት ወሬዎችን በማውራት ህዝብን የማነሳሳት ወንጀል ተከሷል ይላል፡፡
ተከሳሹም በክሱ ላይ ያላቸውን መቃወሚያ ይዘው እንዲቀርቡ ለየካቲት 9 ቀን 2009 የተቀጠሩ ሲሆን ቀደም ሲል በዚሁ ጉዳይ ከፖሊስ ጣቢያ የ5000 ሺ ብር ዋስ አስይዘው የተለቀቁ ሲሆን ከፍ/ቤትም በ1500 ብር ዋስ ተለቀዋል፡፡

Read 1487 times