Saturday, 17 March 2012 10:11

“የእስር ቤቱ ልጅ”፣ “እኔና አንቺ” ይመረቃሉ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ታደሰ ገብረወልድ ጽፎ ያዘጋጀው “የእስር ቤቱ ልጅ” የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ፊልም ነገ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ሲኒማ ቤቶች ይመረቃል፡፡ ይኸንኑ ፊልም በልዩ መርሃግብር ሚያዝያ 1 ቀን 2004 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ለማስመረቅም ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ዘጠኝ ወራት በፈጀው የ105 ደቂቃ ፊልም ላይ አብራር አብዶ፣ አበበ ተምትም፣ ሞገስ ቸኮል፣ መንግስቱ አበበ፣ ግዛቸው መኩርያ፣ ስርጉተማርያም ቅጣው እና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡

በሌላ በኩል “እኔና አንቺ” ፊልም የፊታችን ሰኞ በ11 ሰዓት በአዲስ አበባ ትያትርና ባህል አዳራሽ ይመረቃል፡፡ ፊልሙ ከሁለት ሳምንት በፊት የተመረቀ ሲሆን ያሁኑ ምርቃት ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የ98 ደቂቃ ፊልሙን ሰሎሞን ሙሄ እና ፍቅረ ኢየሱስ ድንበሩ ያዘጋጁት ሲሆን ራሱ ሰሎሞን ሙሄ፣ ማክዳ አፈወርቅ፣ ሊሊ ወርቁ፣ ዮናስ አሰፋ እና ሌሎችም ተውነውበታል፡

 

 

Read 1482 times Last modified on Saturday, 17 March 2012 10:13