Sunday, 05 February 2017 00:00

“ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት” የዛሬ ሳምንት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ዝነኛው ድምጻዊ አብዱ ኪያርና ጃኖ ባንድ የሙዚቃ ሥራቸውን የሚያቀርቡበት ‹‹ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት›› የዛሬ ሳምንት ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በጊዮን ሆቴል ይካሄዳል፡፡ አብዱ ኪያር በመሀሪ ብራዘርስ ባንድ ታጅቦ ታዳሚውን ሲያዝናና፣ጃኖ ባንድ የተለያዩ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ የኮንሰርቱ አዘጋጅ ኢዮሃ አዲስ ኢንተርቴይመንትኤቨንት ለአዲስ አድማስ ጠቁሟል፡፡ ዲጄ ሼሪም ድምፃዊያኑን በማገዝ፣ታዳሚውን በተመረጡ ሙዚቃዎች ሲያዝናና ያመሻል ተብሏል፡፡
የኮንሰርቱን ትኬት ቀድመው ለሚገዙ ኖርማሉ 349 ብር፣ ቪአይፒ 649 ብር የሚሸጥ ሲሆን በዕለቱ ለሚገዙ ኖርማሉ 339 ብር፣ ቪአይፒ ደግሞ 699 ብር እንደሚሸጥ ታውቋል፡፡ የዩኒቨርስቲና የኮሌጅ ተማሪዎች ሁለት ትኬት ሲገዙ፣አንድ ትኬት በነፃ ያገኛሉ ተብሏል፡፡

Read 624 times