Sunday, 05 February 2017 00:00

በደራሲ ስብሀት መጻህፍት ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 እናት የማስታወቂያ ስራዎች ድርጅት ከጎተ ኢንስቲትዩትና ከወመዘክር ጋር በመተባበር ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ የአንጋፋው ደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር የፈጠራ ስራዎች በሆኑት ‹‹ሌቱም አይነጋልኝ”፣ ‹‹ትኩሳት›› እና ‹ሰባተኛው መልዓክ›› መጻህፍት ላይ ውይይት ያካሂዳል፡፡ለውይይት የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የስነ-ፅሁፍ ባለሙያዋ ስነ-ህይወት ገዛኸኝ ሲሆኑ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ አዘጋጆቹ ጋብዘዋል፡፡

Read 693 times