Saturday, 17 March 2012 10:14

ተስፋአብ ዳካ” የግጥም መድበል እና “አልፋና ኦሜጋ ቁጥር 2” ተመረቁ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በአለሚቱ ዳመና የተፃፉ ግጥሞች የተካተቱበት “ተስፋአብ ዳካ” የግጥም መድበል ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ትያትርና ባህል አዳራሽ ተመረቀ፡፡ ለገጣሚዋ ሁለተኛ የሆነው ይሄ መጽሐፍ፤ 95 ገፆች ያሉት ሲሆን ዋጋው 20 ብር ነው፡፡ አለሚቱ ከዚህ ቀደም “ባትጋራኝ” የተሰኘ የግጥም መድበል አሳትማለች፡፡

በሌላ በኩል ዶ/ር አቡሽ አያሌው ያዘጋጁት “አልፋና ኦሜጋ ቁጥር 2” የሥነሕዋ ሳይንስ መፅሐፍ፣ ባለፈው እሁድ የኢትዮጵያ ኅዋ ሳይንስ ማህበር የበላይ ጠባቂ አቶ ተፈራ ዋልዋ እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በራስ አምባ ሆቴል ተመረቀ፡፡ ስለ አልበርት አንስታይን፣ ስለ ሕዋ የሚነሱ አወዛጋቢ ጥያቄዎች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በተዳሰሱበት የመጽሐፍ ምረቃ ላይ ማህበሩ ባዘጋጃቸው አራት ቴሌስኮፖች የጠፈር ጉብኝት ተከናውኗል፡፡

 

 

Read 1278 times Last modified on Saturday, 17 March 2012 10:16