በጥሩ ምንጭ ኪሩቤል የቀረበው “ምኞቴ” የግጥም መጽሐፍ ታትሞ ለገበያ ቀረበ፡፡ 93 ገፆች ያሉት መጽሐፍ 55 ግጥሞች የያዘ ሲሆን ዋጋው 20 ብር ነው፡፡ አብዛኛውን ግጥም ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መታሰቢያ ያደረገው መጽሐፍ፤ ዛሬ በራስ አምባ ሆቴል ይመረቃል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ “ስደት በጋዜጠኛው ዓይን” የተሰኘ መፅሃፍ ታትሞ ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡ ማህበራዊ ፖለቲካ ላይ ያተኮረው መጽሐፉ በ13 ክፍሎች በርካታ ርእሰ ጉዳዮችን ዳስሷል፡፡ የመጽሐፉ ደራሲ ነቢዩ ኢያሱ ካሁን ቀደም “አፍሪካና አምባገነን መሪዎቿ” ፣ “አረቦችና እስራኤል”፣ የእስራኤል የስለላ ውጤት” እና “የሕሊና ባርነት” የሚሉ መፃሕፍት ለንባብ አብቅቷል፡፡