Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 March 2012 10:24

የህፃናት ጥግ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ውድ እግዚአብሔር፡-

አንተ ነህ መብረቅ የምትልክብን? እኔ እኮ ሲጮህ በጣም ነው የሚያስፈራኝ፡፡ እባክህ አቁምልን፡፡

ቶም

ውድ እግዚአብሔር

እግሬን እንደ ጓደኞቼ ጠንካራ ልታደርግልኝ ትችላለህ? እኔም እንደነሱ እግር ኳስ መጫወት እፈልጋለሁ፡፡ ጓደኞቼ ደግሞ ሁልጊዜ ያሾፉብኛል፡፡ በናትህ ተው በላቸው፡፡

ፒተር

ውድ እግዚአብሔር፡-

የሰንበት ት/ቤት መምህሬ ሁልጊዜ “እግዚአብሔር ይወድሻል” ትለኛለች፡፡  እውነቷን ነው? ትላንት ሣራ ላይ የሰራሁትን ብነግርህ ግን ትጠላኝ ነበር፡፡ ወይስ እሱንም ታውቃለህ? እባክህ ይቅርታ አድርግልኝና እንደድሮው ውደደኝ፡፡

ሮዚ

ውድ እግዚአብሔር፡-

አስተማሪዬ ጨካኝ ናት፡፡ ሁልጊዜ ትጮህብኛለች፡፡ ደሞ አሮጊትና አስቀያሚ ናት፡፡ ለምንድነው መጥፎና ጨካኝ ሰዎችን የምትፈጥረው?

ሳሚ

ውድ እግዚአብሔር፡-

አልጋዬ ላይ እየሸናሁ በየቀኑ እገረፋለሁ፡፡ እባክህን ሁለተኛ እንዳልሸና አድርገኝ፡፡

ዴቭ

ውድ እግዚአብሔር፡-

ማክሰኞ ዕለት የስፔሊንግ ፈተና አለብኝ፡፡ ግን ምንም አላውቅም፡፡ ለአሁን ብቻ ትረዳኛለህ? ይሄ ኩረጃ ይባላል እንዴ?

ፓፒ

ውድ እግዚአብሔር፡-

በዓይን አትታይም የሚባለው እውነት ነው? ወይስ አስማት እየሰራህ ነው?

ጆሲ

ውድ እግዚአብሔር፡-

ሁልጊዜ ሰዎች እየሞቱ አዳዲስ ሰዎች ይፈጠራሉ፡ አዳዲስ ሰዎች ከምትፈጥር ለምን ያሉትን አታኖራቸውም?

ሳራ

ውድ እግዚአብሔር፡-

በቀደም ሰርግ ሄጄ ሙሽሮቹ ቤ/ክርስቲያን ውስጥ ሲሳሳሙ አየሁ፡፡ ይቻላል እንዴ?

ጆን

ውድ እግዚአብሔር፡-

ህፃን ወንድም ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ እኔ የፀለይኩት ግን ቡችላ እንድትሰጠኝ ነበር፡፡

ማይክ

 

 

Read 4482 times Last modified on Saturday, 17 March 2012 10:28