Saturday, 18 February 2017 13:54

“ራዕይ” ከዱባይ ንግድ ምክር ቤት መጻህፍት ተለገሰለት

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ራዕይ የህፃናትና ቤተሰብ ልማት ማህበር፣ከዱባይ ንግድ ምክር ቤት 60 ሺህ ብር ደደማ የሚያወጡ መጻህፍትና ደብተሮች ተበረከተለት፡፡ ባለፈው ረቡዕ በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት፤ የዱባይ ንግድ ምክር ቤት፣የኢትዮጵያ
ተወካይ አምባሳደር ተክለአብ አረጋዊ በተገኙበት የርክክብ ስነስርዓቱ ተካሂዷል፡፡ በምክር ቤቱ የተበረከቱት መፅሀፍትና ደብተሮች ማህበሩ በነፃ ለሚደግፋቸውና ለሚያስተምራቸው 347 ተማሪዎች ቤተ-መፅሀፍት በበቂ ሁኔታ ለማደራጀት ይጠቅማል ብለዋል፡፡
   የራዕይ የህፃናትና የቤተሰብ ልማት ማህበር መስራችና ዳሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት ጉልሳ ተናግረዋል፡፡ የዱባይ ንግድ ም/ቤት 2017 ዓ.ም በዱባይ ት/ቤቶች የንባብ ዓመት እንዲሆን በወሰነው መሰረት የዘንድሮውን ዓመት
ስጦታቸውን ለራዕይ አካዳሚ ማበርከታቸውን የምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ተክለአብ አረጋዊ ተናግረዋል፡፡ ራዕይ የህፃናትና የቤተሰብ ልማት ማህበር ላለፉት 10 ዓመታት ወላጆችቸው በችግርና በህመም ውስጥ የሚኖሩ 347 ህፃናትን ተቀብሎ በማስተማርና ቁርስና ምሳ በመመገብ ሲተጋ መቆየቱም በዕለቱ ተገልጿል፡፡

Read 809 times