Saturday, 18 February 2017 14:17

የጡት ካንሰር - 90% ሴቶች፣ 10% ወንዶች

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

 ለሰዎች ጤና መታወክ ምክንያት የሚሆኑ የተለያዩ ባህሪዎች፣ አኗኗሮች፣ አመጋገቦች ወይንም የምቾት አጠባበቅና በተለያዩ ምክንያቶች መንገላታት የመሳሰሉት የሚጠቀሱ ሲሆን ቀደም ባሉት ዘመናት ምክንያታቸው ባልታወቀ ሁኔታ ለሚከሰቱ ሕመሞችም መፍትሔውን ማግኘት አስቸጋሪ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። ከእነዚህም ሕመሞች መካከል የጡት ካንሰር ይገኝበታል። የጡት ካንሰር መኖሩ ሲታወቅ ረጅም ዘመን የሆነው ቢሆንም ምንነቱ እና ሕክምናውን ማግኘት ግን ትግልን የጠየቀ ነበር። ከክርሰቶስ ልደት በፊት በ1500 አመተ አለም ግብጻውያን የህክምና ባለ ሙያዎች ፓፒረስ ላይ ያሰፈሩት የኤድሚን ስሚዝ የቀዶ ጥገና መጽሐፍ ላይ ስለጡት ካንሰር ያሰፈሩት መረጃ አስቀድሞ ከታወቁ የካንሰር ሕመሞች መካከል ቀዳሚው ለመሆኑ እማኝ ነው። በጊዜው ምርምሩን ለማድረግ በናሙናነት የተወሰዱት ሴቶች ቁጥር ስምንት ነበር። እነዚህም ሴቶች ጡታቸው ላይ የህመም ስሜት የነበራቸው ሲሆን የተገኘባቸውም እጢ ነበር። በዚህ ምክንያት በሽታው ምን እንደሆነ ለመታወቅ ጊዜ ባይፈጅበትም በሌላ በኩል ደግሞ መድሀኒት የለውም ተብሎ የተተወ ነበር። ይህም ለበርካታ አመታት ቀጥሎ የቆየ መፍትሔ የለሽ ሕመም ነበር። ሕመሙም በምን ምክንያት ይከሰታል የሚለውንም በጊ ዜው የነበሩ ተመራማሪዎች አልደረሱባቸውም ነበር። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት የጡት ካንሰር በተለይም በእድገት ወደኋላ በቀሩት የአለማችን ክፍሎች ገዳይነቱ እንዳለ ቢሆንም እንደሕመም ከተቆጠረ እና መፍትሔው ከተገኘ ግን አመታትን አሳልፎአል።
የጡት ካንሰር ወንዶችንም ይይዛል ቢባልም በአብዛኛው ግን የሴቶች ሕመም ነው። ሴቶች 90%  ያህል ታማሚ ሲሆኑ ወንዶቹ ግን 10% ያህል ይታመማሉ። ስለዚህም፡-
እድሜ፣ ሴት መሆንና በቤተሰብ ውስጥ የቅርብ ዝምድና እናት፣ እህት፣ ልጅ የጡት ካንሰር ታማሚዎች ከሆኑ በጡት ካንሰር ለመያዝ እድሉን ያሰፋዋል፡ :
ስለዚህ የጡት ካንሰር በብዛት የሚታየው ሴቶች ላይ ነው። ሴቶች ጡታቸው መጠኑ ትልቅ መሆኑ አንዱ ምክንያት ሲሆን የወንዶች ጡት ግን በመጠንም ትንሽ ሰለሆነ በካንሰር የመያዝ እድሉ በጣም ጠባብ ነው። አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም የወንዶች የጡት መጠን በአይን የማይታይና በእጅ የማይዳሰስ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል። ሴቶች በተፈጥሮአቸው ጡታቸው ላይ ብዙ ሴሎች የሚገኙ ሲሆን ወንዶች ግን እንደጡታቸው ማነስ ሴሎቹም ትንሽ “†¨<። ሴሎች በተፈጥሮአቸው መፈጠር፣ ማደግና መሞት የሚል የጊዜ ቀመር አላቸው። ነገር ግን ሴሎቹ በካንሰር በሽታ ሲያዙ ይህ በተፈጥሮ የተመደበላቸው የአኗኗር ባህርይ ይለወጣል። አኗኗራቸውም ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል። ስለዚህ በጡቱ እና በአካባቢው ላይ ያልተለመደ እና የማይታወቅ ክስተት ሊፈጠር ይችላል። ጡትእና አካባቢው ላይ እብጠት ሊታይ ይችላል። ሌሎችም በጡት ጫፍ እና በብብት ስር ሁሉ የተለያዩ ምልክቶች እንዲሁም ፈሳሽ በጡት ጫፉ የመውጣት ነገር ሊከሰት ይችላል። ሁልጊዜም ባይሆንም ግን እንደዚህ ያለ ተፈጥሮአዊ ነገር ሲከሰት የጡት ካንሰር ጀመረ ሊባል ይችላል። እብጠቱም ጊዜ እየጨመረ በሄደ ቁጥር እያደገ በመሄድ ለዳሰሳም አስቸጋሪ ከማይሆንበት በግልጽ ከሚታወቅበት ደረጃ ይደርሳል።
የጡት ካንሰር እዚህ ቦታ ሳይባል በአካባቢው ሁሉም የቱት ክፍል ላይ ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ነገር ግን በአብዛኛው ማለትም 60% ያህል የጡት ካንሰር የሚያድገው በብብት ስር ነው። አንዳንድ ጊዜ ካንሰር ሴሎቹ መሰራራጨት ሲጀምሩ ጡቱ ላይ ከሚያብጠው እጢ በተጨማሪ እጅ ስር ያሉት እጢዎች አብረው ማበጥ ይጀምራራሉ። በግዜ ካልተደረሰበት በጣም ሲያድጉ ወደሌሎች የሰውነት ክፍሎች ይሄዳሉ። ለምሳሌ ሳንባ ላይ ሲሄድ ሳል፣ ደም የቀላቀለ አክታ፣ የደረት ውጋት፣ አየር ማስወጣትና ማስገባትን መከልከል የመሳሰለውን ጉዳት ያስከትላል። የካንሰር ሴል ወደ አጥንት ከሄደ በተለይም ጀርባ ላይ ያለው አከርካሪ አጥንት ላይ ከፍተኛ ሕመም ያስከትላል። ስለዚህ በጡት አካባቢ እብጠት እስኪያድግ መጠበቅ ሳይሆን አስቀድሞውኑ ክትትል በማድረግ እርምጃ መውሰድ ይገባል።
የጡት ካንሰር ከእብጠት ውጪ ሌላ ምንም አይነት ምልክትም ይሁን ስሜት ስለሌለው አስቀድሞ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እብጠቱ ገና ከአንድ ሳንቲ ሜትር በታች እያለ በአንዳንድ ምርመራራዎች ማወቅ ሲቻል ከአንድ እስከሁለት ሴንቲ ሜትር ሲደርስ ግን በዳሰሳ ማወቅ ይቻላል። በዚህ ደረጃ ያለ የካንሰር እጢ ገና ያልተሰራራጨ እና ማዳን የሚቻል ነው። ስለዚህም ነው ከእብጠት ውጪ ሌላ ምልክት ስለሌለው ሴቶች እድሜያቸው ከአርባ አመት ከዘለለ እብጠት ቢኖርም ባይኖርም በየአመቱ ምርመራራ አድርጎ ሁኔታውን ማወቅ ያስፈልጋል የሚባለው።
 የጡት ካንሰር ከእብጠት ውጪ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም ብሎ መደምደም ግን አይቻልም። አልፎ አልፎ ማለትም ከመቶ አስር ያህል ታማሚዎች የተለያየ ስሜትን ይገል ጻሉ። ለምሳሌም ... ጡት ላይ የህመም ስሜት አለኝ ወይንም ወተት በሚወጣበት ጫፍ ላይ ፈሳሽ ይታየኛል የመሳሰሉትን። ከዚህም በተጨማሪ አንዳንዴ ጡት መጠኑንና ቅርጹን እንደቀየረና በቆዳውም ላይ እንደፈሳሽ ወይንም ቆዳው ላይ አንደሚፈርጥ የሚመስሉ ነገሮች ይታያሉ... ደም መሳይ ነገር አገኘሁበት የሚሉ ምክንያቶችም ይናገራራሉ። ምንም አይነት ምክን ያቶች ቢኖሩም ግን በጊዜው ህክምና ከተደረገለት የማይድንበት ምንም ምክንያት እንደማይኖር ልብ ሊባል ይገባል። ችግር አለው የሚባለው ምናልባት ውስጥ ውስጡን በተለያዩ አካሉች ላይ ሲሰራራጭ ነው። አንዳንድ ጊዜም በጣም ችላ ከተባለ ጡቱ ላይ ያለው እጢ እያደገ ሲመጣ እዛው ጡቱ ላይ ይቆስላል። ያ ከሆነ ኢንፌክሽን በመፍጠር ሽታ ያለው ፈሳሽ እና ደም ያመጣል። ለዚህም የሚሰጠው ሕክምና ቀደም ሲል በተቀመጠው ደረጃ መሰረት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሆነ ኦፕራራሲዮን እንዲሁም ኬሞራራፒ መስጠት እና እንደአስፈላጊነቱ የጨረር ሕክምና ማድረግ ሲሆን እንደምግብ የሚያገለግሉ ሆርሞኖች በተለይም ኢስትሮጂን የሚባለው ከሰውነት ውስጥ እንዲጠፋ የሚዋጥ መድሀኒት ይሰጣል። ኦፕራራሲዮኑ የትኛውም ሆስፒታል ሊሰጥ የሚችል ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዋናው ችግር ሕክምናው ያለመኖሩ ሳይሆን ህክም ናው የሚሰጥባቸው ቦታዎች ያለመስፋፋታቸው። የጡት ካንሰር ደረጃ አለው። ደረጃውም ከአንድ እስከ አራራት ይከፈላል።
1 ኛ ደረጃ የሚባለው የጡት ካንሰር መጠኑ እጅግ ያነሰና በጡት ላይ ብቻ ያበጠ እጢ ነው።
2ኛ ደረጃ የሚባለው የጡት ካንሰር ጡት ላይ ያለው እጢም አደግ ይላል። እንደገናም ብብት ስር እብጠቶቹ ሊዳሰሱ ይችላሉ።
3ኛ ደረጃ የሚባለው የጡት ካንሰር ጡት ላይ ያለው እጢም ትልቅ ሲሆን ብብት ስር እና ዙሪያውን ያሉት እጢዎችም በጣም ጠንንራ እና ያደጉ ሆነው ይዳሰሳሉ።
4ኛ ደረጃ የሚባለው የጡት ካንሰር ከጡትም ከብብት ስርም አልፎ ወደሌሎች የሰውነት ክፍሎች የተሰራጩ ሲሆን ነው።
 ከ1995 ዓ/ም እና ከ2000 ዓ/ም በፊት እንደአውሮፓውያኑ የጊዜ አቆጣጠር የጡት ካንሰር አደገኛ ነበር። በቅርብ ጊዜ ግን በመላው አለም ኢትዮጵያን ጨምሮ የጡት ካንሰርን ማዳን ተችሎአል። ስለዚህም ደረጃ አንድ እና ሁለትን ማዳን ወይንም በደንብ መቆጣጠር ከሚቻልበት የህክምና ጥበብ ተደርሶአል። ደረጃ ሶስትና አራት ትንሽ የሚከብዱ እና ማዳን ባይቻልም እድገ ታቸውን ግን መግታት ተችሎአል። በሕክምናው እርዳታም ሕይወትን በደንብ ማራዘም ይቻላል። (ምንጭ ዶ/ር አበበ በቀለ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ)
የጡት ካንሰርን በሚመለከት በአለም ላይ ታዋቂ የሆነ ሪቫን አለ። ሱዛን ጂ ኮመን ፋውንዴሽን መቀመጫው ኒውዮርክ የነበረ ሲሆን እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1991 ዓ/ም የጡት ካንሰር በሽታን ተቋቁመው ከበሽታው ነጻ ለሆኑ ሰዎች በተዘጋጀው ውድድር ላይ ለተሳታፊዎች ሪቫኑ ከተበተነ ወዲህ ሪቫኑን መጠቀም ልማድ ሆኖአል። ከዚያ ወዲህም ፒንክ ሪቫን እንደአውሮፓ ውያኑ አቆጣጠር ከ1992 ዓ/ም ጀምሮ ሰፊ እውቅና ተሰጥቶት የብሔራዊ የጡት ካንሰር ግንዛቤ መፍጠሪያ ልዩ መለያ ሆኖአል።
የጡት ካንሰርን ግንዛቤ ለማስፋት እንዲረዳ እውን የሆነው ፒንክ ቀለም ሪቫን ሀሳቡ የተወሰደው ለኤችአይቪ ኤይድስ ከተሰራው ቀይ ሪቫን ነበር። ፒንክ ሪቫን በአሌክሳንደራ ፔልና ከጡት ካንሰር በሽታ የዳነችው ኤቭለን ላውደር የተፈጠረ ሲሆን በመላው ኒውዮርክ እንዲሰራጭ ትላልቅ ለሆኑ የኮስሞቲክስ ኩባንያዎች ነበር የተሰጠው። ፒንክ ሪቫን ከሰማያዊ ሪቫን ጋር አብሮ ሲደረግ አጋጣሚው በጣም ጥቂት ቢሆንም በወንዶች ላይ ስለሚከሰተው የጡት ካንሰር አመላካች ይሆናል። የፒንክ ሪቫን ቀለም ፒንክ የሆነበት ምክንያት በምእራባውያን ሐገሮች በስነጾታ የሴቶችን ተሳትፎ የሚገልጹበት በመሆኑ ቀለሙ ሌሎችን ስለመንከባከብ የሚያስረዳ በመሆኑ፣ ቆንጆ መሆንን ስለሚያመላክት፣ ጥሩና ተባባሪ መሆንን ስለሚገልጽ ተብሎ በመታመኑ ነው።
ፒንክ ሪቫን ሲወሳ በጡት ካንሰር ላለመያዝ መፍራት ከተያዙም ለወደፊቱ ተስፋ እንዲያደርጉና የጡት ካንሰር በሽታን የማጥፋት ንቅናቄን ያሳስባል። በጡት ካንሰር ላይ የሚሰሩ የተለያዩ ተቋማት ስራቸውን ከጡት ካንሰር ጋር ይበልጥ ለማቆራኘት ሪቫኑን ይጠቀሙበታል። ፒንክ ሪቫንን መግዛት ማድረግ ወይንም ለእይታ ማብቃት ስለሴቶች ያለውን ክብካቤና ጥንቃቄ ያሳያል የሚል ትርጓሜ ያሰጣል። በተለያዩ አገራት በየአመቱ ጥቅምት ወር ምርቶች በፒንክ ሪቫን ይወከላሉ ወይንም ፒንክ ቀለም እንዲኖራቸው ይደረጋል። ከምርቶቹም ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ የተወሰነውን ስለጡት ካንሰር ለሚደረገው ምርምር ወይንም ግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴ ላይ እንዲውል ይደረጋል።

Read 3912 times