Saturday, 25 February 2017 13:12

‹‹የአድዋ ውሎ ታሪክ›› መፅሐፍ ላይ ነገ ውይይት ይደረጋል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ‹‹የአድዋ ውሎ›› በተሰኘው የደጅ  አዝማች ገ/ማሪያም ጋሪ አጭር የህይወት ታሪክና የአድዋ ውሎ ላይ በሚያተኩረው መፅሐፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት ‹‹ያልተዘመረላቸው›› ቅፅ 1 እና 2 መፅሀፍ ደራሲና የታሪክ ባለሙያ ፍፁም ወ/ማሪያም ሲሆኑ የውይይቱ መድረክ በቋንቋ መምህሩና በታሪክ ባለሙያው ሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሚመራ ተገልጿል፡፡ የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው በዚህ ውይይት ላይ ፍላጎት ያለው እንዲሳተፍም ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡

Read 798 times