ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ‹‹የአድዋ ውሎ›› በተሰኘው የደጅ አዝማች ገ/ማሪያም ጋሪ አጭር የህይወት ታሪክና የአድዋ ውሎ ላይ በሚያተኩረው መፅሐፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት ‹‹ያልተዘመረላቸው›› ቅፅ 1 እና 2 መፅሀፍ ደራሲና የታሪክ ባለሙያ ፍፁም ወ/ማሪያም ሲሆኑ የውይይቱ መድረክ በቋንቋ መምህሩና በታሪክ ባለሙያው ሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሚመራ ተገልጿል፡፡ የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው በዚህ ውይይት ላይ ፍላጎት ያለው እንዲሳተፍም ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡