Sunday, 26 February 2017 00:00

‹‹የህገ መንግስቱ ፈረሰኞች›› ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

 በአረና እና በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ባለው የፖለቲካ ተሳትፎ የሚታወቀው አስራት አብርሀም ‹‹የህገ-መንግስቱ ፈረሰኞች›› የተሰኘ ፖለቲካዊ መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ አበቃ፡፡ ፀሐፊው በዋናነት አሁን በስራ ላይ ያለውን ህገ-መንግስት ማዕከል ያደረገ፣ በህገ-መንግስቱ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉትን በርካታ ጉዳዮች የዳሰሰበት መፅሀፉ፣ በተለይ የህገ-መንግስቱን አርቃቂዎች ማንነት፣ የህገ- መንግስቱን አፀዳደቅ፣ የባንዲራ ጉዳይ፣ ብሄራዊ መዝሙር፣ የክልሎች አወቃቀር፣ በሴቶች እኩልነትና የጋብቻ መብት፣ የመሬት ጉዳይና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እየደረሰ ያለውን ተፅዕኖ አጉልቶ ያሳየበት ነው ተብሏል፡፡ በ200 ገፆች የተመጠነው ይሄው መፅሀፍ ሰሞኑን በ69 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡

Read 2879 times