የኢትዮጵያ ሴት ሯጮች ባላቸው ወቅታዊ ብቃት ከፍተኛ ብልጫ እንደሚያሳዩ ግምት ተሰጥቷል፡፡የዱባይ ማራቶን አሸናፊዋ አሰለፈች መርጊያን ጨምሮ ገነት ጌታነህ፣ ማሚቱ ደስቃ፣ፍሬህይወት ዳዶ፤ አሹ ካሲምና ብዙነሽ ዳባ ይወዳደራሉ፡፡ በወንዶች ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተሳታፊ ገብረእግዚአብሄር ገብረማርያም ነው፡፡ ከኬንያ አትሌቶች ከባድ ፉክክር ይጠብቀዋል፡፡ ገብረእግዚአብሄር ከ2 ዓመት በፊት የኒውዮርክ ማራቶንን ያሸነፈ ሲሆን አምና ደግሞ በቦስተን ማራቶን 3ኛ ደረጃ በማግኘት በ2 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ53 ሴኮንድ በሆነ ጊዜ የግሉን ፈጣን ሰዓት አስመዝግቧል፡፡በተያያዘ በለንደን ማራቶን ፀጋዬ ከበደ፣ ፈይሳ ሌሊሳ፤ በዙ ወርቁ ማርቆስ ገነቴና አብርሃም ጨርቆሴ በወንዶች ምድብ ተሳታፊ ናቸው፡፡ በሴቶች ደግሞ አፀደ ባይሳ ፤እጅጋየሁ ዲባባ፣ ኮረኒ ጀሊላ ፤ብዙነሽ በቀለና አበሩ ከበደ ይሮጣሉ፡፡ በሁለቱ ትልልቅ የማራቶን ውድድሮች በኦሎምፒክ የማራቶን ቡድን ለመካተት ኢትዮጵያውያኑ ከኬንያውያን ብቻ ሳይሆን እርሰራሳቸውም ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡