Saturday, 17 March 2012 11:03

“ፍቅር ... ምክንያቱ አይታወቅም”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(4 votes)

 

በዚህ እትም  ለአንባቢዎች ያልነው ትዳርን ጠንከር ባለ መንፈስ ለመምራት የሚያስችሉ የስነ ልቡና
ምሁራን የሚመክሩዋቸውን ነጥቦች ከተለያዩ መረጃዎች በማሰባሰብ ነው፡፡ በትዳር መካከል
አለመግባባትን ሊፈጥሩ የሚችሉ አንዳንድ ነጥቦችንና በፍቅር ዙሪያ ለጠቅላላ እውቀት የሚረዱ
ሀሳቦችን ለንባብ እነሆ እንላለን፡፡ ምንጮቻችን Bob Strauss እና  Laura Schaefer የተባሉ
ሳይኮሎጂስቶች ናቸው፡፡
በትዳር መካከል ሊፈጠር የሚችል ጭቅጭቅ፡-
ብዙዎች እንደሚያስቡት የተመሰረተ ትዳር ለተጋቢዎቹ የወደፊት ሕይወት ዘለቄታነት ያለው ግንኙነት
እንደሚሆንና ምናልባትም ትዳርን ሊለያይ የሚችለው ሞት ብቻ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ነገር ግን
ከፍቅር ባሻገር ኑሮን በመምራቱ፣ ቤተሰብን በማስተዳደሩ በኩል የተለያዩ አለመግባባቶች እና
ጭቅጭቆች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ በትዳር መካከል የረዘመና መቋጫው የማይታወቅ ጭቅጭቅ የሚፈጠር
ከሆነ ምንም እንኩዋን የተመሰረተው ትዳር ለረዥም ጊዜ እንደሚዘልቅ ቢታሰብም ጭቅጭቁ እየዋለ
እያደር ግን ትዳርን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑ አስቀድሞውኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡
ችግሮችን ቀለል አድርጎ ማየት፡-
በባለትዳሮች ዘንድ ለሚነሱ ጥቃቅን ለሚመስሉ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ነገ ዛሬ ማለት እና
ነገሮችን በአናሳነት በመፈረጅ መፍትሔውን በፍጥነት አለመፈለግ አልፎ አልፎ ያጋጥማል፡፡ በሌላም
በኩል ለተነሱ ነገሮች መፍትሔ ለመስጠት በሚል አንዳቸው ከአንዳቸው ለጊዜው እራቅ ወደ አለ ቦታ
ዞር ማለትን የሚመርጡበት ሁኔታ ይስተ ዋላል፡፡ ይህ ክስተት ምናልባት ነገሩን በስፋት ለማሰብ እና
እራስን ለማረጋጋት ለጊዜው ይረዳ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለተነሳው ጭቅጭቅ መፍትሔ
የሚሻው ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ባለመሰጠቱ ለምን ይህ ሆነ በሚል ቁጭትና ንዴትን
እንዲያብ ሰለስል እንዲሁም ወደከፋ ውሳኔ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በባልና
ሚስቱ መካከል ለተነሱ ጭቅጭቆች ወይንም አለመግባባቶች መፍትሔ ተሰጥ ቶአቸው ያልተቋጩ
ነገሮች  የተረሱ ቢመስሉም እንኩዋን ውለው አድረው ግን ከሌላ ነገር ጋር ተያይዘው መነሳታቸው
ስለማይቀር ስር ለሰደደ መቃቃር ሊዳርግ ይችላል፡፡
ከላይ ለተጠቀሱት አጋጣሚዎች በመፍትሔነት የተጠቆሙት ባልና ሚስቱ አስቀድሞውን ጋብቻ
ከመመስረታቸው በፊት ነገሮችን በምን መንገድ ሊያስተናግዱ እንደሚገባቸው ፕላን ሊያደርጉ
እንደሚገባቸው ነው ፡፡ በገንዘብ ጉዳይ... ቤተሰብን በማስተዳደር ...ዘመድ አዝማድ ...ጉዋደኛን
በምን መልክ ማስተናገድ እንደሚገባ እንዲ ሁም ማንን መርዳት ...ማንን አለመርዳት... የመሳሰሉት
ሁሉ ለውይይት መቅረብ የሚገባቸው እና ለተጋቢዎቹ ቀላል የማይባሉ ናቸው፡፡ ትዳር ሲመሰረት
ንብረት ስለማፍራት ፣ ኃብት ስለማከማቸት ፣ልጅ ስለመውለድ የመሳሰሉት ሲታቀዱ በባህርይ በኩል
ያለው ነገር ግን ብዙ ጊዜ ቸል የሚባል ነው፡፡ ነገር ግን ወደታቀደው ግብ የሚያደርሰው በባህርይ
መግባባት ሲኖር መሆኑ ሊዘነጋ እንደማይገባው ምሁራኑ ያስረዳሉ፡፡
አቋምን አለማስተካከልና ውበትን አለመጠበቅ፡-
በትዳር መካከል አለመግባባቶችን ሊፈጥሩ ከሚችሉ መካከል የራስን አቋምና ውበትን አለማስተካከል
አንዱ ነው፡፡ ሰዎች በትዳር አለም ለረዥም ጊዜያት ሲቆዩ አንዳቸው አንዳቸውን በድርጊታቸው
፣በአለባበሳቸው ፣በአቋማቸው ተጉዋዳኛቸውን ለመማረክ ሲጥሩ ሌላኛው ወገን ደግሞ ከነጭርሱም
ለራሳቸው ትኩረት ላይሰጡ ይችላሉ፡፡ እንደተገኝ ለብሶ መውጣት፣ የገላን ንጽህና አለመጠበቅ፣
የጸጉርን የመሳሰሉ ውበቶችን አለመጠበቅ ሊኖር ይችላል፡፡ የእራስን ንጽህና አለመጠበቅና አቋምን
አለማስ ተካከል ባልታሰበ ሁኔታ በትዳር ጉዋደኛ ዘንድ የመሰልቸት ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ በስራ ቦታ
፣በመዝናኛ ...ወዘተ በመሳሰሉት ቦታዎች የሚታዩትን ሰዎችም ወደህሳቤ ለማስገ ባትና ወደውጭ
ለመሳብ ሁኔታዎችን ሊያመቻች ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፡፡
“እኔ የምፈልገው ሰው የዛሬውን ሳይሆን የእኔን የጥንት ማንነት የሚረዳ እና የሚያስታውሰውን ነው”
በእርግጥ ይህ አባባል ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ነገር ግን በራስ እምነት ብቻ ተመስርቶ የሌላውን
ስሜት እና ፍላጎት መጉዳት አይገባም፡፡ እራስን መጠበቅ ፣ጸድቶ መገኘት የግልን ጤናም ከመጠበቅ
እና የተጉዋዳኝን ስሜት ከመረዳት አኩዋያ ትክክለኛ ድርጊት ስለሆነ ሁሉም ሊተገብረው የሚገባው
ነገር ነው፡፡
ለእራስ ክብር አለመስጠት፡-
አንድ ሰው እራሱን ባከበረ ቁጥር የሌላውንም ክብር እንደሚጠብቅ እሙን ነው፡፡ በተለይም
በባለትዳሮች ዘንድ እራስን ማክበር ማለት የትዳር ጉዋደኛውን ክበር መጠበቅ መሆኑን ሊገነዘብ
ይገባል፡፡ በአነጋገር፣ በአለባስ፣ በስራ ግንኙነት፣ በማህበራዊ ኑሮ፣ በታማኝነት ...ወዘተ በመሳሰሉት
ሁሉ የእራስን ክብር ለመጠበቅ መሞከር ማለት... አብሮ ለሚኖር እንዲሁም በስራ እና በሌላ አጋጣሚ
ለሚያገኙዋቸው ሁሉ ክብርን እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡
ግልጽነት አለመኖር፡-
ባለትዳሮች አንዳቸው ለአንዳቸው በግልጽ አስተያየት በመስጠት የጎደለውን እንዲያሟሉ እንዲሁም
አንዳቸው ለአንዳቸው የሚያስፈልገውን በማቅረብ እንዲረዳዱና ተመሳሳይ በሆነ አቋም እንዲታዩ ግድ
ይላል፡፡ ባል ወይንም ሚስት ከሁለት አንዳቸው የሚፈልጉት ነገር ካለ በግልጽ እርስ በእርሳቸው
ሊነጋገሩበት ይገባል፡፡ ምንም እንኩዋን ባልና ሚስት ከማንኛውም ሰው በላይ መናበብ ይችላሉ
ቢባልም አንዳንድ ጊዜ ድብቅነት ሊኖር ስለሚ ችል ይህንን ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡  በግልጽ
የመነጋገር ጥቅሙ አንዳቸው ስለአንዳቸው ፍላጎት አስቀድሞ ለመረዳትና ተፈላጊውን ነገር አስቀድሞ
ለማድረግ ይጠቅማል፡፡
ልብ ልንላቸው የሚገቡ፡-
በትዳር መካከል የሚደረግን ንግግርን በጩኸት ሳይሆን በእርጋታ ማድረግ ፣
በፍቅር አብረው የሚኖሩ ሰዎች መሞጋገስ ይገባቸዋል ፡፡
ባል ሚስቱን ወይንም ሚስት ባልዋን ሊያመሰግኑ ይገባል ፡፡
የትዳር አጋርዎ ለሚያደርግልዎት ወይም ለምታደርግልዎት ነገር ማመስገንና ማሞገስ እንዲሁም
በእርጋት ማነጋገር የፍቅር አጋርዎ በእርስዎ ውስጥ ምን ያህል ቦታ እንዳለው /እንዳላት ያስረዳል፡፡
ምስጋናው ሲቀርብ ግን ከልብ በመነጭ ስሜት እውነተኛው መሆን ይባዋል፡፡
ስለፍቅር አንዳንድ ነጥቦች፡-
G
በአምስት አመት ያስረዝማሉ፡፡
በባህሪያቸው ሴታሴት የሆነ ፀባይ ያላቸው ሴቶች ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የፍቅር ግንኙነት
ሊኖራራቸው ይችላል፡፡
በአለም ላይ ካሉ 2/3ኛ የሚሆኑት ሰዎች ፍቅር የሚይዛቸው ለረዥም ጊዜ ከሚያውቁት ሰው ሳይሆን
ወዲያውኑ ካወቁት ሰው ነው፡፡
ፍቅር የሰውነት መረጋጋትን ይጨምራራል፡፡ የነርቭ ሲስተምን ያፋጥናል፡፡
እንደስነልቦና ተመራራማሪዎች ፍቅር የጭንቀት ስሜትን የበለጠ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ የአይን
ብሌን መለጠጥን ያስከትላል፡፡ መዳፍ በላብ የመጠመቅ እንዲሁም የልብ ምት መጨመርን
ይፈጥራራል፡፡
በአለም እስከአሁን ድረስ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ትልቁ እና ውብ የሆነ የፍቅር ስጦታ የታጅመሀል
መስኪድ ነው፡፡ ይህ መስኪድ የህንዱ ንጉስ shajam ለሚስቱ እንደመታሰቢያ ያበረከተላት የፍቅር
መግለጫ ነው፡፡
ዶቭ የተባሉት የወፍ ዘሮች ለፍቅር ቀን (valentine day) እንደበአል ማድመቂያ
ይቆጠራራሉ፡፡እነኚህ የወፍ ዘሮች የእምነት እና የፍቅር መገለጫዎች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡
ምክንያቱም የራራሳቸውን አጋር ካገኙ ስለማይለያዩ ነው፡፡
አንድ ሰው ለምን ይፈቀራል?
በከንፈር፣ በአይን፣ በቁመና ..ወዘተ እንዳይባል ይሄ ፍቅር ሳይሆን ምኞት ነው፡፡
በጉብዝና፣ ስለህይወት በሚኖር የጠለቀ ግንዛቤ ...ወዘተ እንዳይባል ይሄም ፍቅር ሳይሆን አድናቆት
ነው፡፡
ፍቅር ማለት አንድ ሰው ሌላውን ለምን እንደሚመርጥ ወይንም በዚያ ሰው ለምን እንደሚመስጥ
ሳይታወቅ ሲቀር ነው፡፡
“ፍቅር የራሱ ምክንያት አለው፡፡ ያ ምክንያት ደግሞ አይታወቅም”
(Bob Strauss እና Laura Schaefer)

 

በዚህ እትም  ለአንባቢዎች ያልነው ትዳርን ጠንከር ባለ መንፈስ ለመምራት የሚያስችሉ የስነ ልቡና ምሁራን የሚመክሩዋቸውን ነጥቦች ከተለያዩ መረጃዎች በማሰባሰብ ነው፡፡ በትዳር መካከል አለመግባባትን ሊፈጥሩ የሚችሉ አንዳንድ ነጥቦችንና በፍቅር ዙሪያ ለጠቅላላ እውቀት የሚረዱ ሀሳቦችን ለንባብ እነሆ እንላለን፡፡ ምንጮቻችን Bob Strauss እና  Laura Schaefer የተባሉ ሳይኮሎጂስቶች ናቸው፡፡  በትዳር መካከል ሊፈጠር የሚችል ጭቅጭቅ፡- ብዙዎች እንደሚያስቡት የተመሰረተ ትዳር ለተጋቢዎቹ የወደፊት ሕይወት ዘለቄታነት ያለው ግንኙነት እንደሚሆንና ምናልባትም ትዳርን ሊለያይ የሚችለው ሞት ብቻ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ነገር ግን ከፍቅር ባሻገር ኑሮን በመምራቱ፣ ቤተሰብን በማስተዳደሩ በኩል የተለያዩ አለመግባባቶች እና ጭቅጭቆች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡

በትዳር መካከል የረዘመና መቋጫው የማይታወቅ ጭቅጭቅ የሚፈጠር ከሆነ ምንም እንኩዋን የተመሰረተው ትዳር ለረዥም ጊዜ እንደሚዘልቅ ቢታሰብም ጭቅጭቁ እየዋለ እያደር ግን ትዳርን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑ አስቀድሞውኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ችግሮችን ቀለል አድርጎ ማየት፡- በባለትዳሮች ዘንድ ለሚነሱ ጥቃቅን ለሚመስሉ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ነገ ዛሬ ማለት እና ነገሮችን በአናሳነት በመፈረጅ መፍትሔውን በፍጥነት አለመፈለግ አልፎ አልፎ ያጋጥማል፡፡ በሌላም በኩል ለተነሱ ነገሮች መፍትሔ ለመስጠት በሚል አንዳቸው ከአንዳቸው ለጊዜው እራቅ ወደ አለ ቦታ ዞር ማለትን የሚመርጡበት ሁኔታ ይስተ ዋላል፡፡ ይህ ክስተት ምናልባት ነገሩን በስፋት ለማሰብ እና እራስን ለማረጋጋት ለጊዜው ይረዳ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለተነሳው ጭቅጭቅ መፍትሔ የሚሻው ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ባለመሰጠቱ ለምን ይህ ሆነ በሚል ቁጭትና ንዴትን እንዲያብ ሰለስል እንዲሁም ወደከፋ ውሳኔ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በባልና ሚስቱ መካከል ለተነሱ ጭቅጭቆች ወይንም አለመግባባቶች መፍትሔ ተሰጥ ቶአቸው ያልተቋጩ ነገሮች  የተረሱ ቢመስሉም እንኩዋን ውለው አድረው ግን ከሌላ ነገር ጋር ተያይዘው መነሳታቸው ስለማይቀር ስር ለሰደደ መቃቃር ሊዳርግ ይችላል፡፡ ከላይ ለተጠቀሱት አጋጣሚዎች በመፍትሔነት የተጠቆሙት ባልና ሚስቱ አስቀድሞውን ጋብቻ ከመመስረታቸው በፊት ነገሮችን በምን መንገድ ሊያስተናግዱ እንደሚገባቸው ፕላን ሊያደርጉ እንደሚገባቸው ነው ፡፡ በገንዘብ ጉዳይ... ቤተሰብን በማስተዳደር ...ዘመድ አዝማድ ...ጉዋደኛን በምን መልክ ማስተናገድ እንደሚገባ እንዲ ሁም ማንን መርዳት ...ማንን አለመርዳት... የመሳሰሉት ሁሉ ለውይይት መቅረብ የሚገባቸው እና ለተጋቢዎቹ ቀላል የማይባሉ ናቸው፡፡ ትዳር ሲመሰረት ንብረት ስለማፍራት ፣ ኃብት ስለማከማቸት ፣ልጅ ስለመውለድ የመሳሰሉት ሲታቀዱ በባህርይ በኩል ያለው ነገር ግን ብዙ ጊዜ ቸል የሚባል ነው፡፡ ነገር ግን ወደታቀደው ግብ የሚያደርሰው በባህርይ መግባባት ሲኖር መሆኑ ሊዘነጋ እንደማይገባው ምሁራኑ ያስረዳሉ፡፡ አቋምን አለማስተካከልና ውበትን አለመጠበቅ፡-በትዳር መካከል አለመግባባቶችን ሊፈጥሩ ከሚችሉ መካከል የራስን አቋምና ውበትን አለማስተካከል አንዱ ነው፡፡ ሰዎች በትዳር አለም ለረዥም ጊዜያት ሲቆዩ አንዳቸው አንዳቸውን በድርጊታቸው ፣በአለባበሳቸው ፣በአቋማቸው ተጉዋዳኛቸውን ለመማረክ ሲጥሩ ሌላኛው ወገን ደግሞ ከነጭርሱም ለራሳቸው ትኩረት ላይሰጡ ይችላሉ፡፡ እንደተገኝ ለብሶ መውጣት፣ የገላን ንጽህና አለመጠበቅ፣ የጸጉርን የመሳሰሉ ውበቶችን አለመጠበቅ ሊኖር ይችላል፡፡ የእራስን ንጽህና አለመጠበቅና አቋምን አለማስ ተካከል ባልታሰበ ሁኔታ በትዳር ጉዋደኛ ዘንድ የመሰልቸት ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ በስራ ቦታ ፣በመዝናኛ ...ወዘተ በመሳሰሉት ቦታዎች የሚታዩትን ሰዎችም ወደህሳቤ ለማስገ ባትና ወደውጭ ለመሳብ ሁኔታዎችን ሊያመቻች ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፡፡ እኔ የምፈልገው ሰው የዛሬውን ሳይሆን የእኔን የጥንት ማንነት የሚረዳ እና የሚያስታውሰውን ነው” በእርግጥ ይህ አባባል ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ነገር ግን በራስ እምነት ብቻ ተመስርቶ የሌላውን

 

ስሜት እና ፍላጎት መጉዳት አይገባም፡፡ እራስን መጠበቅ ፣ጸድቶ መገኘት የግልን ጤናም ከመጠበቅ እና የተጉዋዳኝን ስሜት ከመረዳት አኩዋያ ትክክለኛ ድርጊት ስለሆነ ሁሉም ሊተገብረው የሚገባው ነገር ነው፡፡ ለእራስ ክብር አለመስጠት፡-አንድ ሰው እራሱን ባከበረ ቁጥር የሌላውንም ክብር እንደሚጠብቅ እሙን ነው፡፡ በተለይም በባለትዳሮች ዘንድ እራስን ማክበር ማለት የትዳር ጉዋደኛውን ክበር መጠበቅ መሆኑን ሊገነዘብ ይገባል፡፡ በአነጋገር፣ በአለባስ፣ በስራ ግንኙነት፣ በማህበራዊ ኑሮ፣ በታማኝነት ...ወዘተ በመሳሰሉት ሁሉ የእራስን ክብር ለመጠበቅ መሞከር ማለት... አብሮ ለሚኖር እንዲሁም በስራ እና በሌላ አጋጣሚ ለሚያገኙዋቸው ሁሉ ክብርን እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡ ግልጽነት አለመኖር፡-ባለትዳሮች አንዳቸው ለአንዳቸው በግልጽ አስተያየት በመስጠት የጎደለውን እንዲያሟሉ እንዲሁም አንዳቸው ለአንዳቸው የሚያስፈልገውን በማቅረብ እንዲረዳዱና ተመሳሳይ በሆነ አቋም እንዲታዩ ግድ ይላል፡፡ ባል ወይንም ሚስት ከሁለት አንዳቸው የሚፈልጉት ነገር ካለ በግልጽ እርስ በእርሳቸው ሊነጋገሩበት ይገባል፡፡ ምንም እንኩዋን ባልና ሚስት ከማንኛውም ሰው በላይ መናበብ ይችላሉ ቢባልም አንዳንድ ጊዜ ድብቅነት ሊኖር ስለሚ ችል ይህንን ማስወገድ ተገቢ ነው፡፡  በግልጽ የመነጋገር ጥቅሙ አንዳቸው ስለአንዳቸው ፍላጎት አስቀድሞ ለመረዳትና ተፈላጊውን ነገር አስቀድሞ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡ ብ ልንላቸው የሚገቡ፡- በትዳር መካከል የሚደረግን ንግግርን በጩኸት ሳይሆን በእርጋታ ማድረግ ፣በፍቅር አብረው የሚኖሩ ሰዎች መሞጋገስ ይገባቸዋል ፡፡ባል ሚስቱን ወይንም ሚስት ባልዋን ሊያመሰግኑ ይገባል ፡፡ የትዳር አጋርዎ ለሚያደርግልዎት ወይም ለምታደርግልዎት ነገር ማመስገንና ማሞገስ እንዲሁም በእርጋት ማነጋገር የፍቅር አጋርዎ በእርስዎ ውስጥ ምን ያህል ቦታ እንዳለው /እንዳላት ያስረዳል፡፡ ምስጋናው ሲቀርብ ግን ከልብ በመነጭ ስሜት እውነተኛው መሆን ይባዋል፡፡ ስለፍቅር አንዳንድ ነጥቦች፡-  G

ወዲያውኑ ካወቁት ሰው ነው፡፡ ፍቅር የሰውነት መረጋጋትን ይጨምራራል፡፡ የነርቭ ሲስተምን ያፋጥናል፡፡ እንደስነልቦና ተመራራማሪዎች ፍቅር የጭንቀት ስሜትን የበለጠ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ የአይን ብሌን መለጠጥን ያስከትላል፡፡ መዳፍ በላብ የመጠመቅ እንዲሁም የልብ ምት መጨመርን ይፈጥራራል፡፡ በአለም እስከአሁን ድረስ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ትልቁ እና ውብ የሆነ የፍቅር ስጦታ የታጅመሀል መስኪድ ነው፡፡ ይህ መስኪድ የህንዱ ንጉስ shajam ለሚስቱ እንደመታሰቢያ ያበረከተላት የፍቅር መግለጫ ነው፡፡ ዶቭ የተባሉት የወፍ ዘሮች ለፍቅርቀን(valentine day) እንደበአል ማድመቂያ ይቆጠራራሉ፡፡እነኚህ የወፍ ዘሮች የእምነት እና የፍቅር መገለጫዎች ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ምክንያቱም የራራሳቸውን አጋር ካገኙ ስለማይለያዩ ነው፡፡ አንድ ሰው ለምን ይፈቀራል?በከንፈር፣ በአይን፣ በቁመና ..ወዘተ እንዳይባል ይሄ ፍቅር ሳይሆን ምኞት ነው፡፡በጉብዝና፣ ስለህይወት በሚኖር የጠለቀ ግንዛቤ ...ወዘተ እንዳይባል ይሄም ፍቅር ሳይሆን አድናቆት ነው፡፡ፍቅር ማለት አንድ ሰው ሌላውን ለምን እንደሚመርጥ ወይንም በዚያ ሰው ለምን እንደሚመስጥ ሳይታወቅ ሲቀር ነው፡፡

“ፍቅር የራሱ ምክንያት አለው፡፡ ያ ምክንያት ደግሞ አይታወቅም”

(Bob Strauss እና Laura Schaefer)

 

 

Read 7925 times