Thursday, 09 March 2017 07:50

“ሆድ ይፍጀው... ብዬ”

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

   እኔ በልጅነቴ ነበር አክስቴ ወደምትኖርበት ውጭ ሀገር ሄጄ የሰው ቤት ስራ እንድሰራ ሁኔታዎች የተመቻቹልኝ። የዚህም ምክንያት በትዳር አለም ስኖር ሁለት ልጆችን ከወለድሁ በሁዋላ ባለቤ በመሞቱ ነበር። በሁዋላም ወደውጭ ሀገር ሄጄ ስራዬን በመስራት ላይ እንዳለሁ የአሰሪዬ ዘመድ የሆነ ሀብታም ለትዳር እፈልጋታለሁ በማለቱ ተዳርኩለት። በዚህ ሁኔታ እንዳለን ታሪኬን አጫወትኩት። ልጆቼን ወስጄም እንዳስተምራቸው ፈቀደልኝ። በደስታ ወደምኖርበት ሀገር ወስጄ ሁለቱንም ትምህርት ቤት አስገባሁዋቸው። ሲውል ሲያድርም ልጆቹ አደጉ። አማረባቸው። በተለይም ሴትዋ በጣም ውብ ሆነች። ሰው ማንን ይመስላል ሲባል ኑሮውን ...ተብሎ የለ? ነገር ግን ሁኔታዎች መልካቸውን እየቀየሩ መምጣታቸው አልቀረም። ባለቤ ልጄን አስገድዶ ደፈራት። እኔም ኡኡ የአገር ያለህ አልል...ያለሁት እሰው ሀገር...ማን ሰሚ ይኖረኛል? እንዲሁ እዬዬ እያልኩ ያገናኙንን ሰዎች ሽምግልና ብልክበት...እኔ ልጅ እፈልጋለሁ። እስዋ ደግሞ አልወልድልህም ብላኛለች...ስለዚህ ...በቃ ...እክሳለሁ...አለ። እኔም ለጊዜው ልጄን ይዤ ወደሐገር ቤት መጣሁ። እውነትም ጸንሳ ኖሮአልና ምንም ማድረግ አልቻልኩም። በ17/አመት እድሜዋ የተደፈረችውን ልጄን የጸነሰችውን ልጅም በሰላም ተገላግላ እንድታሳድግ በሚል ተለመንኩና... የተሰጠኝን ካሳ ተቀብዬ ...ሆድ ይፍጀው...ብዬ እንደገና ልጄን ለባሌ በሕግ አፈራርሜ ዳርኩለት። እሱዋም በመጀመሪያው ወንድ ልጅ ከዚያም ሴት ልጅዋን ወልዳ ትዳር ከተባለ ትዳርዋን ይዛ ቁጭ ብላለች። አኔም ከሀያ አመት በላይ ከኖርኩባት ሀገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ትቼ ወደሀገር ቤት ተመልሻለሁ። አያሳዝንም?
 ወ/ሮ ፈትለወርቅ ከአዲስ አበባ።
አለምአቀፉ (Behavioral social and movement sciences ) በ2014 አንድ ጥናት አውጥቶአል። ይህ ጥናት እንደሚገልጸውም አስገድዶ መድፈር በአሁኑ ወቅት አለም አቀፍ ችግር እንደሆነ ነው። እንዲያውም ጥናቱ እንደሚገልጸው ካለጥርጥር በአለማችን እየተካሄዱ ካሉ ጦርነቶች እንደአ ንዱ ሊቆጠር ይችላል። ምንም እንኩዋን በሴቶች መብት ላይ አመታትን ያስቆጠረ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችና ንቃተ ሕሊናን የሚያዳብሩ ስራዎች ቢሰሩም ዛሬም ሴቶችንና ልጃገረዶችን የመድፈር ሁኔታ በመቀጠሉ እንደ አንዱ የስነዋልዶ ጤና ችግር መንስኤ ሆኖ ከማስቸገሩም በላይ ምናልባትም ከህብረተሰቡ ማግኘት የሚገባውን የመከላከል ስራም አላገኘም ማለት ይቻላል ይላል ጥናቱ። በእርግጥ አስገድዶ መድፈር ከቦታ ቦታ እና እንደየህብረተሰቡ የኑሮ ልምድ እና እንደየሀገራቱ የህግ አተረጉዋጎም የተለያየ ትርጉም የሚሰጠው ነው። በአጠቃላይ ግን አስገድዶ መድፈር ወንድ በሴት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት የከፋ ሆኖ ቢታይም ሴቶችም አልፎ አልፎ በወንዶች ላይ የሚፈጽሙት ሆኖ ይስተዋላል። ወደጥናቱ ዝርዝር ስንገባ በመጀመሪያ የአስገድዶ መድፈር ሁኔታ እና የደፋሪዎች ማንነት ይቀድማል።
የአስገድዶ መድፈር እና የደፋሪዎች አይነት
Zanni(2009) ዛኒ የተባለች ተመራማሪ ለአለም የጤና ድርጅት ባቀረበችው ምርምር እንደገለጸ ችው ጥቃት አድራሾች በተለያዩ ቡድኖች ይከፈላሉ ትላለች።
Stranger Rape - በማይተዋወቁ ሰዎች መካከል የሚደርስ የጾታዊ ጥቃት አይነት ነው። ይህም ማለት ጥቃት አድራሹም ሆነ ጥቃት የሚፈጸምበት ሰው ቀደም ሲል ምንም አይነት ትውውቅ የሌላቸውና በአጋጣሚ የሚፈጸም ነገር መሆኑን ነው።
Acquaintance rape - ጥቃት አድራሹ እና ጥቃት የሚፈጸምበት ሰው አስቀድሞውኑ ትውውቅ ያላቸውና ያንን መሰረት በማድረግም የሚፈጸም ነው። ይህ ትውውቅም ምናልባትም በቀድሞው ጊዜ እጮኛነት ወይንም የፍቅር ግንኙነት የነበራቸው እንዲሁም የግብረስጋ ግንኙነት አድርገው የሚያውቁ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
Partner rape - አብረው በሚኖሩ ሰዎች መካከል የሚፈጸም ነው። ሁለቱ ሰዎች አብረውየኖሩት በባልና ሚስትነት ሊሆን ይችላል። ወይንም በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ወይንም በስራ አጋጣሚ በአንድ ጣሪያ ስር የሚኖሩ ሊሆኑ ይችላሉ። በኑሮ አጋጣሚም በቤት ውስጥ በዘመዳሞች መካከል የሚፈጠር አስገድዶ መድፈር ሊሆን ይችላል።
Gang Rape - ሌላው አስገድዶ መድፈር የመፈጸም ሁኔታ የተወሰኑ ወንዶች በቡድን ሆነው የሚፈጽሙት ነው። ይሄም ሰዎቹ ለምንድነው እንዲህ ያለ ጥቃት የሚፈጽሙት ተብሎ ሲጠየቅ በልጅነት ዘመናቸው ወይንም ደጉም በሁዋላ በህብረት ወንጀል መፈጸ ምን እያዳበሩ የመጡ መሆናቸውን ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት። በአባቢ፣ በዘር ወይንም በትምህርት ቤት በመሳሰሉት እነእገሌ እኮ ኃይለኞች ወይንም ጎበዞች ናቸው ተዋጊዎች ናቸው የሚል አይነት መገለጫን እያዳበሩ የመጡ ሰዎች ናቸው አስገድዶ መድፈር ወንጀልን የሚፈጽሙት። እንደዚህ ያለው ወንጀል በተለያዩ የአፍሪ አገሮችና በሌሎችም የሚታይ ነው። አንዱ ሌላውን ከመዋጋት ይልቅ የተቃራኒውን ወገን አስገድዶ በመድፈር ሃይልን መወጣት ይበልጥ የሚያስደስትበት ሁኔታ ይታያል።
የተለያዩ መረጃዎች እንደሚገልጹት አልኮሆል ወይንም ሱስ አስያዥ እጽን መጠቀም አንዱ ለአስገድዶ መድፈር የሚዳርግ ነገር ነው። ሰዎች በተፈጥሮ ህብረተሰቡ የሰጠውን ሁኔታ ተቀብሎ በማደግ ያልሆነ ነገር ውስጥ እንዳይገቡ የሚመልሳቸው በጭንቅላት ውስጥ የሚገኝ ተፈጥሮአዊ ነገር አለ። ያ ተፈጥሮአዊ ነገር ድርጊትን ለመፈጸም በሚፈለግበት ጊዜ ይሄ ትክ ክል አይደለም ይሄ ትክክል ነው የሚል ከመጥፎ ነገር የሚከላከለ ነው። አልኮሆል ወይንም ሱስ አስያዥ ንጥረ ነገር ግን ይህንን ጥሩና መጥፎ ነገር አመላካች የሆነውን ነገር በማደብዘዝ ይገታዋል። ስለሆነም ይህንን ነገር ማድረግ የለብኝም ያስቀጣኛል ወይንም ሰው እጎዳለሁ ወይ ንም ህብረተሰቡ ይህንን ድርጊት ያወግዘዋል ብሎ ለመተው ከመሞከር ይልቅ እንዲያውም ድርጊቱን ለመፈጸም የሚገፋፋ የሚያደፋፍር ነገር ይፈጠራል።
ወንድ ሴትን የሚደፍረው ብዙ ጊዜ የስርአተ ጾታ ክፍፍል ልዩነቱ ወይንም ጀንደር ከሚለው ሁኔታ ጋር ይያያዛል። ሴት እንዲህ ነች ወንድ ደግሞ እንዲህ ነው የሚለውን ህብረተሰቡ የሚያምንበትና ተግባራዊ እያደረገው ለው ጋር በተያያዘ አስገድዶ መድፈሩ ብዙ ጊዜ ይፈጸማል። ምክንያቱም ህብረተሰቡ ለወንድ ልጅ ኃይል ወይንም አቅም እንዳለው እየነገረ ስለሚያሳድገው ወንዱ በተፈጥሮው ገኘው ጥንሬ ባሻገር በአስተሳሰብም ኃይል እንዲኖረው ያደርገዋል።ከዚህም በተለየም በልጅነታቸው የመደፈር ወይንም የመገለል እንዲሁም የተለያዩ ጥቃቶች የደረሰባቸው ከሆነ አስገድዶ መድፈርን እንደ እልህ መወጫ ይጠቀሙበታል። አንድ ወንድ እንደዚህ ያለ ጉዳት እየደረሰበት ያደገ ከሆነና እሱም ጥቃቱን መፈጸሙ በሳይንሳዊው መንገድ ሲተረጎም አእምሮው በሚያድግበት ሰአት የተለያዩ ኢንዛይሞች ማለትም ነርቭ ከነርቭ የሚገናኝበት መልእክት የማስተላለፊያ ኬሚሎች በደም ውስጥ እየቀነሰ ይመጣል። አእምሮው እያደገ ሲመጣ ደሙ ግን እየቀነሰ መምጣቱ በሚያድጉበት ሰአት ላይ ይህንን ወሲባዊ ጥቃትም ሆነ ማንኛውንም ወንጀል እንደሰው መግደል የመሳሰሉትን ጨምሮ የመፈጸም እድላቸው የሰፋ ይሆናል። ብዙ ጊዜ አስገድዶ መድፈር የሚፈጽሙ ሰዎች ከአንድ ሰው ጋር ወይንም ከተለያዩ ሰዎች ጋር ጥሩ አይነት ግንኙነት መመስረት የማይችሉ ናቸው። ይህ እንግዲህ ከአስተዳደግ ወይንም ከተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎች ሊሆን ይችላል። በተረጋጋ ሁኔታ ከሰዎች ጋር መኖር ልተቻለ ወይንም ህብረተሰቡ የሚጠብቀውን ደረጃ ማሟላት ልተቻለ እንደመሸሻ የሚቆጠረው የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን የመሳሰሉ ሊሆኑ ይችላሉ።
 ዶ/ር ዳዊት ደሳለኝ
 የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት
Alexis (2009) እንደምትገልጸው የወሲብ ጥቃት አድራሾች ወይንም አስገድደው ደፋሪዎች በሶስት ይከፈላሉ።
Power rapist :- ጉልበት የማሳየት ወይንም እኔ ከእገሌ እበልጣለሁ ስለዚህም ማሳየት አለብኝ ከሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ የሚመነጭ ሲሆን የሚረኩትም ጾታዊ ግንኙነት በማድረጋቸው ሳይሆን የበላይነትን በማሳየታቸው ነው።
Opportunist rapists:- የሚባሉት ደግሞ የሚፈልጉዋትን ሴት ለረጅም ጊዜ ሲከታተሉ ቆይተው ሁኔታዎች ሲፈቅዱ የወሲብ ጥቃት የሚያደርሱ ናቸው።
Entitlement rapists :- የሚባሉት ደግሞ ሴትዋ ፈለገችም አልፈለገችም ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ የወንድ ልጅ መብቱ ነው ብለው የሚያስቡ ናቸው።
“አስገድዶ መድፈርን የሚፈጽሙት ወንዶች የግብረስጋ ግንኙነትን ፈልገው ሳይሆን ኃይልን ለመግለጽ የሚያደርጉ ሲሆን በዚሁ አጋጣሚ ግን አንዳንድ ጊዜ ሴቶች ተገደው እየተደፈሩ ሳሉ ወደ ወሲባዊ ስሜት የሚገቡበት ሁኔታ መኖሩም ተረጋግጦአል።
ሴቶቹ በዚህ ስሜት ምክንያት ማለትም ተገድጄ እየተደፈርኩ ግን ደስተኛ ሆንኩ በሚል ብዙ ጊዜ እራሳቸውን ያማርራሉ። ነገር ግን እንዲህ ያለው ነገር የሚከሰተው ስሜቱ ከተፈጥሮ ቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ነው። ይሄ ሁሉም ተገደው የሚደፈሩ ሴቶች ላይ የሚኖር ሳይሆን አንዳንድ ሴቶች ላይ የሚፈጠር ነው። ወንዶቹም አስገድደው በሚደፍሩበት ጊዜ ኃይላቸውን አሳይተው ይተዋሉ እንጂ የዘር ፈሳሽ እስኪለቁ ድረስ ወሲባዊ ግንኙነቱን እያደረጉ አይቆዩም።”
ዶ/ር ዳዊት ደሳለኝ
የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት

Read 2770 times