Monday, 06 March 2017 00:00

የዳንስ ትርኢት ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(2 votes)

 በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚሰሩ የ26 ድርጅቶች ጥምረት የሆነው “የኢትዮጵያ ናሽናል ዲሴቢሊቲ አክሽን ኔትወርክ (ኢንዳን)” የዓለም የሴቶች ቀንን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ የፊታችን አርብ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባህል ማዕከል የአካል ጉዳተኛ ሴቶች የዳንስ ትርኢት ያቀርባል፡፡  ለግማሽ ቀን በሚቆየው በዚህ የሴቶች ቀን አከባበር ላይ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ያለባቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸውን የሚመለከቱ ጥናታዊ ፅሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን በፅሁፎቹ ላይ ውይይትና ሌሎች ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶችም ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

Read 955 times