Saturday, 11 March 2017 11:58

ቃና ቴሌቪዥን የህፃናት ፊልም በአማርኛ ሊጀምር ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 የውጭ ሀገር ፊልሞችን በአማርኛ ተርጉሞ በማቅረብ የሚታወቀው ቃና ቴሌቪዥን፤ የህፃናት ካርቱን ፊልሞችን በአማርኛ ተርጉሞ ሊያቀርብ ነው፡፡ ከ15 በላይ ሀገሮች በመታየት ተወዳጅነትን አትርፏል የተባለውንና በተከታታይ ሲቀርብ ከ50 አመት በላይ ያስቆጠረውን “ኡሞ” የተሰኘ የአሻንጉሊት ፊልም ከመጪው ሚያዚያ ጀምሮ እንደሚያቀርብ ጣቢያው አስታውቋል፡፡ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተመልሶ የተዘጋጀው ፊልሙ፤ የኢትዮጵያውያንን ህፃናት ባህልና ማህበረሰባዊ እሴት የጠበቀ መሆኑን የቃና ቴሌቪዥን ኃላፊዎች አስታውቀዋል፡፡ ከተመሰረተ ዓመት ያልሞላው ቃና ቴሌቪዥን፤ 180 ያህል ባለሙያዎች ቀጥሮ እያሰራ ሲሆን አሁን እየቀረቡ ካሉት ፊልሞችና ፕሮግራሞች በተጨማሪ በቅርቡ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ይፋ እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2208 times