Saturday, 11 March 2017 12:08

‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ ጥያቄዎችና ባህሎች›› ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ ከኢትዮጲስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ ጥያቄዎችና ባህሎች›› በተሰኘው የዶ/ር ኃብተማሪያም አሰፋ መፅሀፍ ላይ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቤተ-
መፃህፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡
   ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት ጋዜጠኛና የታሪክ ተመራማሪ ታዲዮስ ታንቱ እንደሆኑ የገለፀው ሚዩዚክ ሜይዴይ፤ መድረኩ በታሪክ ባለሙያው ሰለሞን ተሰማ ጂ. እንደሚመራ ጠቁሟል፡፡ በውይይቱ ላይ ፍላጎት ያለው ሁሉ እንዲሳተፍ አዘጋጁ ጋብዟል፡፡

Read 1501 times