Monday, 20 March 2017 00:00

“የሰርቆ አደሮች ስብሰባና ሌሎችም” ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(10 votes)

በእውቁ የሀይማኖት ተመራማሪና ወግ ፀሐፊ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተዘጋጀው “የሰርቆ አደሮች ስብሰባና ሌሎችም” የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሀፉ ከ20 በላይ አጫጭር ወጎችን ያካተተ ሲሆን መታሰቢያነቱም የአድዋ ድል በዓልን ለማክበር ከአዲስ አበባ አድዋ ድረስ በእግራቸው ለሚጓዙት ወጣቶች (ጉዞ አድዋ) መሆኑ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ተገልጿል፡፡ በአግዮስ ህትመትና ጠቅላላ የንግድ ስራ አሳታሚነት እየተከፋፈለ የሚገኘው መፅሐፉ፤ በ211 ገጾች ተቀንብቦ በ70 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 3127 times