Monday, 20 March 2017 00:00

“ኑ እንደንስ” የዳንስ ትርኢት ተካሄደ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ከአሜሪካ የመጣው ኬግዊን ፕላስ ካምፓኒ የዳንስ ቡድንና የተለያዩ የኢትዮጵያ የዳንስ ቡድኖች የተሳተፉበት “ኑ እንደንስ” የዳንስ ትርኢት ባለፈው ሳምንት አጋማሽ በብሄራዊ ቴአትር አዳራሽ ተካሄደ። በዳንስ ሞሽን ዩኤስኤ በቀረበውና የአሜሪካ ኤምባሲ ባስተባበረው በዚህ የዳንስ ትርኢት ላይ ከአሜሪካው “ኬግዊን” የዳንስ ቡድን በተጨማሪ “ኢትዮጵያዊነት”፣ “ሚዩዚክ ሜይዴይ”፣ “ሀሁ” እና ሌሎችም የዳንስ ቡድኖች ስራዎቻቸውን
አቅርበውበታል፡፡ በትርኢቱ ላይ ባህላዊ፣ ዘመናዊና የፍቅር ዳንሶች ለታዳሚው የቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም ሁሉም የዳንስ ቡድኖች በጋራ በመደነስ ትርኢቱ ተጠናቀቋል፡፡

Read 1694 times