Monday, 20 March 2017 00:00

ኢራን ኤምባሲ ሰኞ የግጥም ምሽት ያካሂዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   የዓለም የሥነ ግጥም ቀንን ለማክበር ነው

       በአዲስ አበባ የሚገኘው የኢራን ኤምባሲ የባህል ማዕከል የዓለም የሥነ ግጥም ቀንን ምክንያት በማድረግ ከነገ ወዲያ ሰኞ ከ11፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል አዳራሽ የግጥም ምሽት ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡በምሽቱ ዝግጅት ላይ ወጣትና ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶችና ገጣሚያን የፐርሽያን ግጥሞችና የራሳቸውን ሥራዎች የሚያቀርቡ ሲሆን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ 100 ገደማ እንግዶችና የግጥም አፍቃሪያን እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ዓለም አቀፉ የሥነ ግጥም ቀን የሚከበረው ዩኔስኮ እ.ኤ.አ በ1999 በፓሪስ ባካሄደው 30ኛ ጉባኤው ላይ ማርች 21 የዓለም የሥነ ግጥም ቀን ሆኖ እንዲከበር ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑ ይታወቃል፡፡

Read 2182 times