Print this page
Monday, 20 March 2017 00:00

ጋና 110 ሚኒስትሮችን ለሹመት ማጨቷ አነጋጋሪ ሆኗል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሚኒስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮች የተካተቱበትንና 110 ያህል ዕጩዎች የተካተቱበትን ዝርዝር ባለፈው ረዕቡ ይፋ ማድረጋቸው አነጋጋሪ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይፋ ባደረጉት የዕጩ ሚኒስትሮች ዝርዝር የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴርን ጨምሮ አምስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እያንዳንዳቸው ሶስት ምክትል ሚኒስትሮች እንደሚኖራቸው የተገለጸ ሲሆን  የአገሪቱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች “አዲሱ ሹመት የህዝቡን ገንዘብ የሚበሉ ሆዳሞችን ቁጥር ከማብዛት ባለፈ ፋይዳ የለውም” ሲሉ ሃሳቡን ተችተውታል፡፡
በርካታ ጋናውያን ፕሬዚዳንቱ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ሚኒስትሮችን በዕጩነት ማቅረባቸውን በተለያዩ ድረገጾች እያጣጣሉት እንደሚገኙ የጠቆመው ዘገባው፤ የአገሪቱ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሙስጠፋ ሃሚድ ግን፣ መንግስት በርካታ ሚኒስትሮችን መሾሙ የተያዘውን ሰፊ የልማት ዕቅድ በማስፈጸም ረገድ ትልቅ አቅም ይፈጥራልና ሊተች አይገባውም ብለዋል፡፡

Read 1483 times
Administrator

Latest from Administrator