Saturday, 18 March 2017 16:05

የህጻናት ጥቃት! በደል!.

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

“እንደተነገረኝ ከሆነ ገና ሕጻን እያለሁ ነበር አባ የሞተው። እናም ኑሮዋን መግፋት ስላልቻለች ሌላ ሰው አገባች። አንድ ልጅ ከወለደችለት በሁዋላ በመካከላቸው ከፍተኛ ጸብ የሰፈነበት ሕየወት መምራት ለእና ግዴታ ነበር። ነጋ ጠባ ጭቅጭቅ ነው። ድብድብ ነው። እና እንደነገረችኝ ገና የስምንት ልጅ ሳለሁ የእንጀራ አባ እናን ሲደበድባት በድንጋጤ እየጮህኩ መሀከላቸው ስገባ ለእና የሰነዘረው እርግጫ እኔ ላይ ነበር ያረፈው። ከአቅሜም በላይ ስለነበር ሞታለች ብላ እና ስታለቅስ ጎረቤቶች ተሩዋሩጠው ወደሆስፒታል ያደርሱኛል። ለወር ያህል ሆስፒታል ተኝቼ ስወጣ ለእና የተነገራት በማህጸኔ አካባቢ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰብኝና ለጊዜው እንድታከም ለወደፊቱ ደግሞ ሁኔታውን መከታተል እንደሚገባ ነበር። እናም በዚህ ምክንያት ከባልዋ ተፋትታ የጉልት ስራ ኑሮዋን ቀጠለች። በዚህ ኑሮዋም እናን ለማገዝ በሚል የሸክም እና ሌሎች ከባድ ስራዎችን እሳተፍ ነበር። በዚህ ምክንየት ይሁን በሌላ ... ብቻ በማላውቀው ሁኔታ አሁን ልጅ መውለድ አልቻልኩም። ሐኪም ቤት ብሄድም ወደፊት እንደሚሻለኝ ነግረው ሕክምና አድርገው ይሸኙኛል። አኔ ግን ያሳስበኛል። ምክንያቱም እድሜዬ እየጨመረ ሲሄድ የበለጠውኑ ችግር እንዳይገጥመኝ እፈራለሁ።” ... ሶስና በላይ ከአማኑኤል
ሕጻናት በሙሉ ጤንነት እና ደህንነት ተጠብቀው የማደግ መብት አላቸው። ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ይህንን መብት አክብረው ካሳደጉዋቸው ልጆች ካለምንም የአካል የስነልቡናና የጤና ችግር ሊያድጉ ይችላሉ። አለበለዚያ ግን የተለያዩ ጥቃቶች ልጆችን ለተለያዩ የስነተዋልዶ አካላት ጤና ጉዳት ሊዳርጉዋ ቸው እንደሚችሉ የሶስና በላይ ደብዳቤ ያሳያል። ለመሆኑ የሕጻናት ጥቃት ሲባል ምን ማለት ነው? የስነልቡና ባለሙያው አቶ መኮንን በለጠ ለዚህ እትም ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ መኮንን በለጠ በቄቈበቂ ቄቃ ቋበቋሮሽቃሮሯቁስ ሰሻሽቁሳ ስቂቅቄብስቈቂስቃ ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ሕጻናት አገልግሎት መስጫ ማአከል አማካሪ ናቸው።
ጥያቄ፡ የህጻናት ጥቃት ወይንም በደል ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ፡ ቃሉም እንደሚያመለክተው የህጻናት ጥቃት ወይንም በደል ማለት አዋቂዎች ወይንም ከእነሱ በእድሜ ከፍ ያሉ ሰዎች ሆን ብለው በማወቅ በሕጻናት ላይ የሚፈጽሙት ድርጊት ሆኖ ሕጻናቶችን ለተለያዩ አካላዊና ስነልቡናዊ ቁስለት ወይንም ጉዳት የሚዳርግ ድርጊት ነው። የተጠኑ ጥናቶችም ይሁኑ ተግባራዊ ተሞክሮዎች የሚያሳዩት በአገር ውስጥም ይሁን በአለም አቀፍ ደረጃ የህጻናት ጥቃትና በደል ወይንም ትኩረትን መነፈግ ብዙ ሕጻናቶችን ጤና ከማሳጣት አልፎ ለህልፈተ ሕይወት የሚዳርግ ነው። የህጻናት ጥቃትና በደል በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ነው።
1/አካላዊ ጥቃት
አካላዊ ጥቃት ማለት ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ወይንም በቅርብ የሚገኙ ሰዎች በሕጻናት ላይ የሚያደርሱት ጥቃት አካላዊ ቁስለትን ፣መድማትን ፣ ስብራትን በሚያሳይ መልኩ ሲፈጸምና የድርጊቱም አፈጻጸም ሕጻናቶችን በጥፊ በመምታት፣ በእርግጫ በመርገጥ እንዲሁም በተለያዩ ግለት ባላቸው መሳሪያዎች ወይንም እሳቶች ማቃጠል ፣የተለያዩ ዱላዎችን በመጠቀም አካላዊ ጉዳት ማድረስ ፣በጥርስ መንከስ፣ በጥፍር መቧጨር፣ ጸጉርን መንጨት ወይንም መላጨት በመሳሰሉት የሚፈጸም ነው።
2/ ስሜታዊ ጥቃት
ስሜታዊ ጥቃት ማለት በህጻናቱ የወደፊት ራእይ አላማና ተስፋ ላይ ተጽእኖ የሚያደርሱ፣ ስሜታቸውን በሚጎዳ ሕሊናቸውን በሚያቆስል መልኩ የተለያዩ ድርጊቶችን መፈጸም ነው። እነዚህ ድርጊቶችም በግድየለሽነት የሚሰነዘሩ ስድቦች፣ ማንቋሸሽ ፣ሕጻናቱን ማዋረድ፣ በማይፈልጉት ቅጽል ስም መጥራት ፣በማያውቁት ነገር ማስፈራራትና ማስደንገጥ የመሳሰሉት የልጆቹን የወደፊት ሕልውና የሚጋፋ ድርጊት ነው። ልጆች ባጠቃላይም ስሜታቸው እንዲጎዳ ተደርጎ ጥቃት ሲደርስባቸው መረበሽ ፣ድብርት ፣ፍርሀት ፣መጥፎ ስሜት የመሰማት ሁኔታ ይታይ ባቸዋል። ሁልጊዜም ሁሉም ነገር አስቸጋሪ እንደሆነ አድርገው የመገንዘብ ነገር ይስተዋል ባቸዋል። ቀድመው በመቆጣት ነገሮችን ይቀበላሉ። በትምህርት ቤት ቅን ተፎካካሪ መሆን ይጎድላቸዋል።
3/ ወሲባዊ ጥቃት
ማንኛውም ሰው ሕጻናትን በማታለል ወይንም በማስገደድ ለፍልጎት ማርኪያ ሲጠቀሙባቸው ወሲባዊ ጥቃት ይባላል። ወሲባዊ ትቃት የደረሰባቸው ልጆች አስቀድመው ጉዳቱ እንደደረሰ ባይገልጹትም እንኩዋን አንዳንድ ምልክቶችን ያሳያሉ። ለምሳሌም በስነተዋልዶ አካላቸው አካባቢ የማሳከክ የመድማት እንዲሁም በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ በሽታዎች ሲይዙዋ ቸው ምናልባትም ልብሳቸው የመቀደድ እና ደም የመንካት ሁኔታ የሚስተዋልበት ከሆነ እና ሞራላቸው ውድቅ ብሎ ለምንም ነገር ግድ የማይሰጣቸው እንዲያውም አደገኛ ወደሆነው የወ ሲብ ግንኙነት አዝማሚያ የሚሄዱ ከሆነ የደረሰባቸውን ጉዳት ማወቅ ስለሚቻል አስቀድሞ ውኑ እርዳት የሚያገኙበትን መንገድ ማፈላለግ ይጠቅማል።
ከላይ የተጠቀሱት በሶስት አይነት የተፈረጁት ጥቃቶች የህጻናት ጥቃት ወይንም በደል ተብለው ይገለጻሉ።
ጥ/ ሕጻናቱን ከጥቃቱ ለማዳን ምን ማድረግ ይበጃል?
መ/ ሕጻናትን እየመቱ ማሳደግ በአገራችን ቆየት ያለ ልማድ ነው። ነገር ግን በቀድሞው ጊዜ የሚደረገው ልጅን ቀጥቶ ለማሳደግ ያህል እንጂ አሁን እንደሚገለጸው ድብደባ በሚባል መልኩ አይደለም። በእርግጥ በቀድሞው ጊዜ ድብደባ የለም አልነበረም ለማለት አይደለም። ልጆችን አስሮ መግረፍ ፣በበርበሬ ማጠን የመሳሰሉት ሁሉ በየዋህነት ልጆችን ድጋሚ ሲያጠፉ ላለመመ ልከት የሚደረጉ ጉዳቶች ነበሩ። ነገር ግን በዚያን ጊዜ የነበረው ልማድ ደብዳቢ ወላጆችን ቤተሰብን አስተማሪዎችን ጭምር ከልጆች ከተማ ሪዎች ጋር ሲያግባባ ቆይቶአል። ምክንያቱም ሳይመታ የሚያድግ ልጅ ስላልነበረ እና ምንም ምርጫ ስላልነበረ ልጆች ተቀብለውት ለወላጆቻቸው ታዛዥ ሆነው ኖረዋል። ልጆች ድብደባ ደረሰባቸው በሚልም ምንም ወቀሳ ሳይሰነዘር እንዲያውም ደብዳቢ ወላጆች ኃይለኞች ፣ጎበዞች ፣ልጆችን በስነምግባር አንጸው የሚያሳድጉ ሲባሉ በሌላ በኩል ደግሞ ልጆቻቸውን የማይመቱ፣ የማያሸማቅቁ ወላጆች ኃላፊነታቸውን እንዳልተወጡ፣ ልጆቻቸውም ስነምግባር የጎደላቸው ተደርገው ሚቆጠሩበት ጊዜ ነበር። ቆየት ባለው ዘመን ልጆች በወላጆቻቸው ወይንም በአስተማሪዎቻቸው ብቻ ሳይሆን በጎረቤት በአካባቢ ህብረተሰብ ጭምር እየተቀጡ ያድጉ የነበረበት ጊዜ አልፎአል። አሁን ያለው ሁኔታ ግን ለየት ያለ ነው። ምክንያቱም ልጆች በመደብደባቸው ምክንያት ለብዙ አይነት የጤና ጉድለት እንደሚዳረጉ እሙን በመሆኑ እና ዘመኑም የህጻናትን መብት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲከበር መንገድ በመፍጠሩ ምክንያት የህጻናት አካላዊና ስነልቡናዊ ጥቃት አግባብ እንዳልሆነ ተሰምሮበታል። ህጻናት መደብደብ እንደሌለባቸውና የህጻናት አእምሮ ከአዋቂዎች አእምሮ በጣም የተሸለ መሆኑም በተለያዩ ጥናቶች ተረጋግጦአል።
1/ ያዩትንና የሰሙትን ነገር በአንድ ጊዜ እንደካሜራ የመቅረጽ ብቃት፡-
 ዱላ ወላጆችም ይሁኑ አሳዳጊዎች የራሳቸውን ችግር መልሶ ለመካስ የሚጠቀሙበት መንገድ ነው። ብዙውን ጊዜ ሕጻናቶች የሚቀርጹት ነገር በአርአያነት የሚቀርቡዋቸው ሰዎች የሚተገብሩትን ነው። በጣም መልካም የሆኑ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ፍቅር ሰጥተው ፍቅር እንዲቀበሉ አክብረውና ትኩረት ሰጥተው ፣ያላቸውን ስሜት ተረድተው አግባብነት ባለው መልኩ በግልጽነትና በምክንያት ያሳደጉዋቸው ልጆች ለዱላ የሚደርስ ችግር አይፈጽሙም። ቢያጠፉም እንኩዋን ከጥፋታቸው የመማር እድላቸው ሰፊ ነው። በተቃራኒው ደግሞ ሕጻናት መልካም ካልሆኑ ወላጆችና አሳዳጊዎች የሚወርሱት ውርስ አለ። ይኼውም ለተፈጸመው ድርጊት ሁሉ ዱላ ማረቂያ ይሆናል የሚል እምነት ካለ ሁሉም ወላጅ ፣ትምህርት ቤት፣ ህብረተሰብ ወይንም መንግስትም ጭምር መጠንቀቅ ያለበት ኃይልና ጉልበት ምላሹ የከፋ መሆኑን ነው። የሚገረፉ ወይንም የሚመቱ ጭንቅላቶች የሚመቱት መመታት ፣መገረፍ እስከሚችሉበት አቅም ድረስ ብቻ ነው። ያንን መቋቋም ሲጀምሩ ምላሻቸው ስድብ ወይንም ዱላ ከዚያም ካለፈ ከቤት መኮብለል ይሆናል። ስለዚህ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝንበት ያይላል።
2/ ህጻናቶች አዋቂዎችን የሚበልጡበት ሌላው መንገድ የሚፈልጉትን እስከሚያገኙ ድረስ ነገሮችን መደጋገማቸው ነው። ይህ ተቀባይነት ባለው ወይንም በሌለው መንገድም ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የሚፈልጉት ነገር መልካምና ሰናይ ነገር ከሆነ ጠይቀው ለጥያቄአቸው መልካም እና አጥጋቢ ምላሽ ካገኙ እርካታቸው ጥግ ድረስ የመሆኑን ያህል ጥያቄአቸው ካልተመለሰ ግን በተደጋጋሚ ጥፋት የመተግበር እድላቸው ሰፊ ነው ። በዚህም ምክንያት ወላጆች በተደጋጋሚ ለሚፈጸመው ጥፋት ምላሻቸው ዱላ ስለሚሆን ዱላው ሲበዛ ደግሞ የአእምሮ መደንዘዝን ፣በግል ተነሳሽነትን ፣የበታችነት ስሜትን ፣በሌሎች ሰዎች ላይ ቁጡ የመሆንን ፣ሕይወትን ማማረርን ፣የውጭ ተጽእኖን አጋንኖ ወደተለያዩ የባህርይ ችግሮች ማምራትን ያመጣል።
3/ ሕጻናት እውነተኛ ምስክሮች ናቸው። የተደረገላቸውን ነገር በፍጥነት የመመለስ ብቃት አላቸው። ለምሳሌም ፍቅር ሰጥተው ፍቅር እንዲቀበሉ የሚያደርግ ቤተሰብ ውስጥ የሚያድጉ ልጆችን በፍቅር የፈለጉትን ነገር ማሰራት ይቻላል። በተቃራኒው ደግሞ በጥላቻ ማእቀፍ ውስጥ በማግለል በስድብ በዱላ ያደጉ ከሆኑ ተበቃይነታቸው የዛኑ ያህል ይሆናል። ስለዚህ ብዙ የወደፊት ተስፋና ራእይ ያላቸው ሕጻናት አእምሮዎች ቀጭጨው ለአልባሌ ድርጊቶች እንዳይዳረጉ ሁሉም ልብ ሊለው ይገባል።

Read 3254 times