Monday, 27 March 2017 00:00

አንብባችሁ እንድትስቁ!!

Written by 
Rate this item
(9 votes)

  አባት ሰዎች ሲዋሹ በጥፊ የሚማታ ውሸት የሚለይ ሮቦት ይገዛል፡፡
አንድ ማታ እራት ላይም ሮቦቱን ሊሞክረው ይወስናል፡፡.
አባት ልጁ ከሰዓት በኋላ ምን ሲሰራ እንደነበር ይጠይቀዋል፡፡
ልጅም “የቤት ሥራ ስሰራ ነበር” ይላል፡፡
ሮቦቱ ልጁን ጥፊ ያቀምሰዋል፡፡
ዋሽቷል ማለት ነው፡፡
“እሺ--እሺ--ጓደኛዬ ቤት ፊልም ስመለከት ነበር” ብሎ ንግግሩን ያርማል፡፡
“ምን ዓይነት ፊልም ነው ስትመለከቱ የነበረው?” አባት ይጠይቃል፡፡
ልጅም፡- “የካርቱን ፊልም”
ሮቦቱ ልጁን በጥፊ ይመታዋል፡፡
“በቃ የወሲብ ፊልም ነው” ይላል ልጅ፡፡
አባትም፡- “ምን አልክ?
እኔ እኮ ባንተ ዕድሜ ወሲብ ምን እንደሆነ እንኳን አላውቅም”
ሮቦት ቀልድ አያውቅም፤ አባትየውን በጥፊ፡፡
እናት ሳቀችና፡- “የአባቱ ልጅ! በራስህ ነው የወጣው” አለች፤ ሳይቸግራት፡፡
ሮቦቱ እናትየውንም በጥፊ አቀመሳት፡፡
ወዲያው ሮቦቱ እንዲሸጥ ተፈረደበት፡፡
***
አንድ ቀን ፈጣሪ ወደ አዳም ዘንድ ብቅ ብሎ፤
“ጥቂት መልካም ዜናና ጥቂት መጥፎ ዜና ልነግርህ ነው የመጣሁት” ይለዋል፡፡
አዳምም ፈጣሪውን ትክ ብሎ ተመለከተና፤ “እንግዲያውስ መልካሙን ዜና አስቀድምልኝ” አለው፡፡
ፈጣሪም ፈገግ አለና ጉዳዩን ማብራራት ጀመረ፡-
“ሁለት አዳዲስ የአካል ክፍሎችን (ኦርጋን) ይዤህልህ መጥቼአለሁ፡፡
 አንደኛው አዕምሮ ይባላል፡፡
በጣም ብልህ እንድትሆን ያደርግሃል፤ አዳዲስ ነገሮችን ለመፍጠርና ከሄዋን ጋርም በአስተውሎት እንድታወጋ ይረዳሃል፡፡
ሌላኛው ያመጣሁልህ የአካል ክፍል ደግሞ ብልት ይባላል፡፡
እንደ ራስህ ብልህ የሆነ አዲስ ህይወት ለመፍጠርና እቺን ፕላኔት በዘርህ ለመሙላት ያስችልሃል፡፡
ለሄዋንም ልጆች ስለምታፈራላት ደስታዋ ይጨምራል፡፡”
አዳምም በደስታ ተጥለቅልቆ የሚሰራው የሚያደርገው ጠፋው፡፡
“በጣም ድንቅ ስጦታዎችን ነው ያበረከትክልኝ፤ ከዚህ ዕጹብ ድንቅ ገጸ በረከት በኋላ ምን ዓይነት መጥፎ ዜና ልትነግረኝ እንደምትችል አይቼ?” አለው ፈጣሪን፡፡
ፈጣሪም፤ “መጥፎው ዜና ምን መሰለህ፣ ስፈጥርህ የሰጠሁህ የደም መጠን እነዚህን ሁለት አካላት (ኦርጋንስ) በአንድ ጊዜ ማሰራት የሚችል አይደለም፤ተራ በተራ እንጂ” አለው በሃዘን ስሜት ተውጦ፡፡
(አንዱ ኦርጋን ሲሰራ አንዱ ሥራ ያቆማል)
*   *   *
ቀኑን ሙሉ የቢራ አምራቾች ጉባኤ ሲካሄድ ይውላል፡፡
ጉባኤው ሲጠናቀቅ የሁሉም ኩባንያዎች ፕሬዚዳንቶች ወደ አንድ መጠጥ ቤት ጎራ ብለው ቢራ ለመጎንጨት ይስማማሉ፡፡
የበድዋይዘር ቢራ ፕሬዚዳንት በድዋይዘር ያዝዛል፡፡ የሚለር ቢራ ፕሬዚዳንትም ሚለር ያዝዛል።
የኩርስ ቢራ ፕሬዚዳንት እንዲሁ ኩርስ ቢራ ያዝዛል፡፡
በመጨረሻም አስተናጋጇ የጊነስ ቢራ ባለቤትና ፕሬዚዳንት የሆነውን አርተር ጊነስን ምን እንደሚጠጣ ትጠይቀዋለች፡፡ ሚስተር ጊነስም፤ “ኮካኮላ” በማለት ሁሉንም አስገረማቸው፡፡
“ጊነስ ቢራ ለምን አላዘዝክም?” ሲሉ ጠየቁት ባልደረቦቹ፡፡
እሱም፡- “እናንተ ቢራ ካልጠጣችሁ እኔም አልጠጣም” ሲል መለሰላቸው፡፡
(ቀላል ነገራቸው!)
*   *   *
አንድ አዲስ አስተማሪ ወደ ክፍል እየገባች ሳለ፣በሳይኮሎጂ ኮርስ የተማረችውን በጥቅም ላይ ለማዋል አሰበች፡፡
እናም የዕለቱን የትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዲህ በማለት ጀመረች፡-
“በዚህ ክፍል ውስጥ ደደብ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሁሉ ተነስቶ ይቁም”
ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ህጻኑ ጆኒ ተነስቶ ይቆማል፡፡
አስተማሪዋም፡- “ጆኒ፤ ደደብ ነኝ ብለህ ታስባለህ?; ጠየቀችው፡፡
“በጭራሽ፤ እርስዎ ብቻዎን መቆምዎ አናዶኝ ነው”
*   *   *
ችግሩ ያለው ማ ጋ ነው?
ሰውየው ሃኪሙ ዘንድ ይሄድና፡-
“የሚስቴ የመስማት አቅም የደከመ ይመስለኛል፤ እንደ ድሮው አይደለም፤ ምን ባደርግ ይሻለኛል?” ሲል ምክር ይጠይቀዋል፡፡
ሃኪሙም፡- “እርግጠኛ ለመሆን ይህን ሞክር፤ ሚስትህ ወጥ ቤት ሆና ምግብ ስታሰናዳ ከኋላዋ 15 ጫማ ርቀት ላይ ሆነህ የሆነ ነገር ጠይቃት፡፡ መልስ ካልሰጠችህ እየቀረብካት መልስ እስክትሰጥህ ድረስ መጠየቅህን ቀጥል” አለው፡፡
ሰውየው ወደ ቤቱ ተመለሰና ሚስቱ እራት ማዘጋጀት ስትጀምር የተባለውን ይሞክር ገባ፡፡
ከኋላዋ 15 ጫማ ርቀት ላይ ቆሞ፤ “ማሬ፤ ዛሬ እራታችን ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት፡፡ ነገር ግን ከሷ ምላሽ አላገኘም፡፡ 10 ጫማ ተጠግቶ በድጋሚ ሚስቱን ጠየቃት፡፡
አሁንም መልስ የለም፡፡
5 ጫማ ቀረበና ጥያቄውን አቀረበ፡፡
ግን ምላሽ አላገኘም፡፡
በመጨረሻ ከኋላዋ ቆሞ፤
“ማሬ÷ዛሬ እራታችን ምንድን ነው?” አላት፡፡
ሚስትም ፡-
“ለአራተኛ  ጊዜ   እነግርሃለሁ፤  
ዶሮ ነው!” አለችው፡፡
ችግሩ ያለው ማ ጋ ነው ? ከእሱ ወይስ ከእሷ?
*   *   *
አንዲት በመካከለኛ ዕድሜዋ ላይ የምትገኝ ሴት በድንገተኛ የልብ ህመም ራሷን ስታ ሆስፒታል ትገባለች፡፡
የቀዶ ህክምና እየተደረገላት ሳለም ነፍሷ ከስጋዋ ተለይታ ሰማይ ቤት ትሄዳለች፡፡
እዚያም እግዚአብሄርን ታገኘውና፤ “ቀኔ ደርሷል እንዴ?” ስትል ትጠይቀዋለች፡፡
እግዚአብሄርም፡- “አልደረሰም ገና 40 ዓመት ከ4 ወር ይቀርሻል” ይላታል፡፡
ከህመሟ ስታገግም ታዲያ እዚያው ለመቆየት ትወስንና የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና እንዲሰራላት ትጠይቃለች፡፡
ብዙ ዕድሜ ስለሚቀራት ዓለሟን ልታይ ተመኝታለች፡፡
እናም ፊቷን አስቀየረች፣ ቦርጯን አስቀነሰች፣ ዳሌዋን ማራኪ እንዲሆን አድርጋ አሰራች፡፡
የጸጉሯንም ቀለም አስቀየረች፡፡
የማታ ማታም አንድ ፍሬ ኮረዳ መስላ ቁጭ አለች፡፡
የምትሻውን መልክና ገጽታ ከተጎናጸፈች በኋላ በደስታ ተጥለቅልቃ ከሆስፒታሉ ወጣች፡፡
ነገር ግን ወደ ቤቷ እየሄደች ሳለ መንገድ ስትሻገር አምቡላንስ ገጭቷት ትሞታለች፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ ከእግዚአብሄር ጋር ስትገናኝም፡-
“ሌላ 40 ዓመት ይቀርሻል ብለኸኝ አልነበር፤ ለምን ከአምቡላንሱ አደጋ አላተረፍከኝም?” ስትል ተቆጥታ ጠየቀችው፡፡
እግዚአብሄርም መለሰላት፡-
“አዝናለሁ፤ አንቺ መሆንሽን አላወቅሁም ነበር”
*   *   *
ሰውየው የቅርብ ጓደኛው ሚስት ሞታ ሊያስተዛዝነው ወደ ቤቱ ይሄዳል፡፡
በሩን ቢቆረቁር ግን የሚከፍትለት ያጣል፡፡ ምን ተፈጠረ በሚል ስጋት በሩን ገፋ አድርጎ ይገባል፡፡
ጓደኛውን ያገኘው ግን ከሌላ ሴት ጋር ሲሳሳም ነበር፡፡
“ጃክ” አለ ሰውየው በመገረም ተሞልቶ÷ “ሚስትህ እኮ ከሞተች ገና 24 ሰዓት አልሞላትም”
ጓደኝየው ቀና ብሎ ተመለከተውና፤ “በዚህ ሃዘን ውስጥ ሆኜ የምሰራውን የማውቅ ይመስልሃል?” አለው፡፡
*   *   *
ባል፡- ሎተሪ ቢደርሰኝ ምን ታደርጊያለሽ?
ሚስት፡- ግማሹን ወስጄ የራሴን ህይወት ለብቻዬ እጀምራለሁ
ባል፡- ይኸውልሽ 100 ዶላር ደርሶኛል፤እባክሽን 50 ዶላርሽን ውሰጂና አሁኑኑ ሂጂልኝ!
*   *   *
የሰላዮች ፈተና -----
የጀርመን፣ የጣሊያንና የሩሲያ ሰላዮች በሥራ ላይ ሳሉ በቁጥጥር ስር ይውሉና ምርመራ ይደረግባቸዋል፡፡
የታሰሩት መስኮት በሌለው ጠባብ ወህኒ ቤት ውስጥ ሲሆን ምግብ የሚሰጣቸው ነፍሳቸውን ለማቆየት ያህል ብቻ ነበር፡፡
መጀመሪያ ለምርመራ የተጠራው የጀርመኑ ሰላይ ነው፡፡
እጆቹ ታስረውና ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር የተመረመረው፡፡
ለሁለት ሰዓት ያህል ድብደባና ስቃዩን ችሎ ለማን እንደሚሰራ ሳይናገር ከቆየ በኋላ የማታ ማታ ተረታ፡፡
ወደ እስር ክፍሉ ሲመለስ ግን ሌሎቹ ሰላዮች ይሄን ያህል ሰዓት መከራውን ችሎ በመቆየቱ አደነቁት፡፡
በመቀጠል የሄደው የሩሲያው ሰላይ ነበር፡፡ እሱ ደግሞ ለ12 ሰዓታት ከፍተኛ ድብደባና ስቃይ ከደረሰበት በኋላ ለማን እንደሚሰራ ተናገረ፡፡ ወደ እስር ክፍሉ ሲመለስም ለዚያ ሁሉ ሰዓታት በጽናት በመቆየቱ ሌሎቹ ሰላዮች በእጅጉ ተደመሙበት፡፡
በመጨረሻም ጣሊያናዊው ሰላይ ወደ ምርመራ ክፍሉ ተላከ፡፡ እጁን ታስሮ ለ4 ቀናት እየተደበደበ ቢሰቃይም ለማን እንደሚሰራ ትንፍሽ ሳይል ወደ እስር ክፍሉ ተመለሰ፡፡ ሌሎቹ ሰላዮች እንዴት ለ4 ቀናት ሳይናገር መቆየት እንደቻለ ጠየቁት፡፡
እሱም፤ “ለመናገር እኮ ሞክሬ ነበር፤ነገር ግን እጆቼን ማንቀሳቀስ አልቻልኩም; አላቸው፡፡
(ጣልያን እጆቹን ካላንቀሳቀሰ ማውራት አይችልም ይባል የለ!)
*   *   *
አባት፡-እኔ የመረጥኩልህን ሴት እንድታገባ እፈልጋለሁ
ልጅ፡- አላደርገውም!
አባት፡- የቢል ጌትስ ልጅ እኮ ናት
ልጅ፡- እንደሱ ከሆነ እሺ
አባት ወደ ቢል ጌትስ ዘንድ ይሄዳሉ፡፡
.አባት፡- ልጅህ ልጄን እንድታገባው እፈልጋለሁ
ቢል ጌትስ፡- ፈጽሞ አይሆንም!
አባት፡- ልጄ እኮ የዓለም ባንክ ዋና ሃላፊ ነው
ቢል ጌትስ፡- እንዲያ ከሆነ እሺ
አባት የዓለም ባንኩ ፕሬዚዳንት ዘንድ ይሄዳሉ፡፡
አባት፡- ልጄን የባንኩ ዋና ሃላፊ አድርገህ ሹምልኝ
ፕሬዚዳንቱ፡- የማይሞከረውን!
አባት፡- ልጄ እኮ ያገባው የቢል ጌትስን ልጅ ነው
ፕሬዚዳንት፡- እንደሱ ከሆነ ይቻላል!
ይሄ ነው እንግዲህ ቢዝነስ ማለት!
*   *   *
አንድ ሩሲያዊ አሜሪካ ኤርፖርት ውስጥ ከቀረጥ ነጻ (duty free shop) መደብር ጎራ ይላል፡፡
የመደብሩን አስተናጋጅም፤ “የሩሲያ ቋንቋ ትችያለሽ?” ሲል ይጠይቃታል፡፡
“አዎ፤ ትንሽ ትንሽ እችላለሁ” መለሰችለት፡፡
ሩሲያዊው “እፎይ” አለና “ማርልቦሮ” አላት፡፡
(ለዚሁ ነው በሬዬን ያረድኩት አለ አበሻ!)
*   *   *
በሩሲያ የት/ቤት ክፍል ውስጥ ነው አሉ፡፡
አስተማሪ፡- ጎበዝ ልጆች ያሉት የት ነው?
ተማሪዎች፡- በሩሲያ!
አስተማሪ፡- ጣፋጭ ከረሜላዎች የት ነው የሚመረቱት?
ተማሪዎች፡- በሩሲያ!
አስተማሪ፡- ምርጥ ከተሞች የት ነው ያሉት?
ተማሪዎች፡- በሩሲያ!
ድንገት በክፍሉ ውስጥ ካሉት ተማሪዎች ትንሷ ናድያ ማልቀስ ጀመረች፡፡
አስተማሪው፡- ናድያ፤ ለምንድን ነው የምታለቅሺው?
ናድያ፡- ሩሲያ የምትባለው አገር መኖር እፈልጋለሁ!
(እኔም ሁሌ የኢቢሲ ጦቢያ ትናፍቀኛለች!)
*   *   *
ወህኒ ቤት ወይስ ት/ቤት?
ቻይና ውስጥ ነው አሉ፡፡ የሆነ ፕሮጀክት ተሰርቶ ከተጠናቀቀ በኋላ በዛ ያለ ገንዘብ ይተርፋል፡፡ የአካባቢው ቋሚ ኮሚቴ ተሰብስቦ የተረፈው ገንዘብ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤትን ለማደስ ይዋል ወይስ ወህኒ ቤት ይታደስበት በሚለው ላይ ይወያያል፡፡ ነገር ግን ወደ አንድ ውሳኔ ለመምጣት አልተቻለም፡፡
በመጨረሻ ግን አንድ በቋሚ ኮሚቴው ውስጥ ለረዥም ጊዜ በአባልነት የቆዩ ሰው ሁሉንም ያስገረመ አስተያየት ሰነዘሩ፡- “በዚህ ዕድሜያችን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የመከታተል ዕድል እናገኛለን እንዴ?”
ለአፍታ ዝምታ ነገሰ፡፡
ከፊሉ ሻይ መጠጣት፣ ከፊሉ ደግሞ ከቅንድቡ ላይ ላቡን መጠራረግ ያዘ፡፡ ከዚያም ሁሉም አባላት “ወህኒ ቤት ይታደስበት” በሚለው ተስማሙ፡፡
(ከዕለታት አንድ ቀን ሁሉም ወህኒ ቤት መግባታቸው አይቀርማ!)
*   *   *
ብላክሜይል!
ትንሹ ሳሚ ለገና ቢስክሌት እንዲገዛለት ለእናቱ ጥያቄ ያቀርባል፡፡ እናቱም ለአባ ገና ደብዳቤ ቢጽፍላቸው እንደሚሻል ትነግረዋለች፡፡ ሳሚ ግን ደብዳቤውን ለህጻኑ ኢየሱስ ብጽፍ እመርጣለሁ አለ፡፡
እናቱም በዚሁ ሃሳብ ተስማማች፡፡
ሳሚ ወደ ክፍሉ በመግባትም እንዲህ ሲል
ጻፈ፡- “ውድ ኢየሱስ፤ በጣም ጥሩ ልጅ ስለሆንኩ ለገና ቢስክሌት እፈልጋለሁ፡፡”
ሆኖም የጻፈውን ደግሞ ሲያነበው ብዙም ሳያስደስተው ቀረ፡፡ ስለዚህም እንደገና ለመጻፍ ሞከረ፡- “ውድ ኢየሱስ፤ አብዛኛውን ጊዜ ጥሩ ልጅ ነኝ፤ እናም ለገና ቢስክሌት እፈልጋለሁ፡፡”
አሁንም ግን ሲያነበው አላስደሰተውም፡፡
ለሦስተኛ ጊዜ ለመጻፍ ሙከራ
አደረገ፡- “ውድ ኢየሱስ፤ አዲስ ቢስክሌት ካገኘሁ ጥሩ ልጅ ለመሆን እሞክራለሁ”
ይሄኛውም የልቡን አላደረሰለትም፡፡
በመጨረሻ የተሻለ ሃሳብ ለማመንጨት በማሰብ፣ ከቤቱ ወጥቶ በእግሩ መጓዝ ይጀምራል፡፡ ጥቂት እንደተጓዘም አንድ መኖሪያ ቤት በረንዳ ላይ በነሀስ የተሰራ ትንሽዬ የድንግል ማርያም ምስል (ቅርጽ) ተሰቅሎ ይመለከታል፡፡ አንድ ሃሳብ ከመቅጽበት ብልጭ አለለት፡፡ ሳሚ በቀጥታ ወደ ቤቱ ያመራና የማርያምን ምስል ከተሰቀለበት አውርዶ ኮቱ ውስጥ በመሸሸግ በጥድፊያ ወደ ቤቱ ያመራል፡፡ እክፍሉ ውስጥ ገብቶም አልጋው ስር ይደብቀዋል፡፡
ከዚያም የሚከተለውን ደብዳቤ ጻፈ፡- ”“ውድ ኢየሱስ፤ እናትህን ዳግም ማየት የምትፈልግ ከሆነ አዲስ ቢስክሌት ላክልኝ”
*   *   *
ቀናተኛዋ ሚስት!
ሚስት በሥራ ላይ ለሚገኘው ባሏ ስልክ ለመደወል ትሞክርና ሞባይሏ ሂሳብ እንደሌለው ትረዳለች፡፡
ወዲያው ትንሹ ልጃቸው በራሱ ሞባይል አባቱ ጋ ደውሎ የፈለገችውን አስቸኳይ መልዕክት እንዲያደርስ ታዘዋለች፡
ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ልጅ ለእናቱ እንዲህ ይላታል፤ “ሶስት ጊዜ ደውዬ ሴት ነው ያነሳችው”
ሚስት ባሏ እስኪመጣ መታገስ አቅቷት በንዴት ስትንቆራጠጥ ትቆይና የመኪናውን ድምጽ ስትሰማ ከቤት ዘላ ትወጣለች፡፡ ከመኪናው ሲወርድ ጠብቃም ምንም ሳትናገር ጥፊ ታቀምሰዋለች፡፡
ባል ተደናግጦ ምክንያቱን ሊጠይቃት ሲል ሌላ ጥፊ ትደግመዋለች፡፡
በዚህም ጠብ ይነሳና ጎረቤት ይሰባሰባል፡፡
ይሄኔ ወደ ልጇ ዞር ትልና አባቱ ጋ ሲደውል ያነሳችው ሴትዮ ምን እንዳለችው ለተሰበሰበው ሰው እንዲናገር ትጠይቀዋለች፡-
ልጁም እንዲህ አለ፡-
“የደወሉላቸው ደንበኛ ከአገልግሎት ጥሪ ውጭ ስለሆኑ እባክዎ ትንሽ ቆይተው ይሞክሩ”
(ሚስት እንዴት ታፍር!

Read 3341 times