Monday, 27 March 2017 00:00

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በራሱ ፕሬስ ያሳተመውን መፅሐፍ ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

የተመሠረተበትን 7ኛ አመት የሚያከብረው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ፣ ራሱ ባቋቋመው የፕሬስ ድርጅት ያሳተመውን መፅሐፍ የፊታችን ሰኞ ከ9 ሰዓት ጀምሮ በማዕከሉ ግቢ ያስመርቃል፡፡ በዕለቱ የሚመረቀው በብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ ተፅፎ፣ በፕ/ር ባህሩ ዘውዴ የተሰናዳው ‹‹የህሩይ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በአውሮፓና በመካከለኛው ምስራቅ” የተሰኘ መፅሃፍ ነው ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ ቀን አካዳሚው ያቋቋመው የባህል ስነ ጥበብ ማዕከልና ወመዘክር ተመርቆ አገልጎሎት መስጠት እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬስ›› በሚል የተቋቋመው አሣታሚው፤ የተለያዩ የምርምርና ሌሎች መፅሐፍትን ለንባብ እንደሚያበቃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1707 times