Monday, 03 April 2017 00:00

“የማዕበል ዋናተኞች” በጄቲቪ ከረቡዕ ጀምሮ ይተላለፋል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

የደራሲ ኃይሉ ፀጋዬ ሥራ የሆነውና ከዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ይተላለፍ የነበረው “የማዕበል ዋናተኞች” ተከታታይ የሬዲዮ ድራማ ወደ ቴሌቪዥን ድራማ የተቀየረ ሲሆን ከፊታችን ረቡዕ ምሽት 3፡00 ጀምሮ በጄቲቪ ኢትዮጵያ መተላለፍ እንደሚጀምር የድራማው ፕሮዱዩሰር አቶ ሙሉቀን ተሾመ ታደሰ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በሬዲዮ ድራማነቱ ጊዜ እንደ ሽመልስ አበራ፣ ኤልሳቤጥ መላኩና መስታወት አራጋውን የመሳሰሉ ድንቅ ተዋንያን ይተውኑበት እንደነበር ያስታወሱት ፕሮዱዩሰሩ፤በአሁኑ ሰዓት ወለላ አሰፋ፣ ዘላለም ብርሃኑ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ ሰሀር አብዱልከሪምና ሌሎችም በርካታ ተዋንያን እንደተሳተፉበት ገልጸል፡፡  በሦስት ሲዝን ተከፍሎ ለአንድ ዓመት ተኩል የሚዘልቀው "የማዕበል ዋናተኞች" የቴሌቪዥን ድራማ፤በሴም አማኑኤል ሀይሌ ዳይሬክት መደረጉ ታውቋል፡፡  

Read 1570 times