Monday, 03 April 2017 00:00

“ግጥምና በገና 3” የሥነ ፅሁፍ ምሽት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(8 votes)

 “ግጥምና በገና 3” የሥነ ፅሁፍ ምሽት የፊታችን አርብ ከምሽቱ 11፡30 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ለሦስተኛ ጊዜ እንደሚካሄድ አዘጋጁ ኢጋ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን                                                አስታወቀ፡፡ በዚህ ምሽት ወጣትና እውቅ ገጣሚያኑ ሰለሞን ሳህለ፣ ደምሰው መርሻ፣ መስፍን ወ/ተንሳይ፣ ምልዕቲ ኪሮስ፣ ረድኤት ተረፈና ሌሎችም ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ የተባለ ሲሆን ከ20 በላይ በሚሆኑ በገና ደርዳሪዎች የግልና የቡድን የበገና ድርደራ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ወግ፣ እንጉርጉሮና ሌሎች ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች በመሶብ የባህል ሙዚቃ ቡድን ታጅበው ለታዳሚ እንደሚቀርቡ ተጠቁሟል

Read 3820 times