Print this page
Saturday, 01 April 2017 14:38

‹‹ከ እስከ›› መፅሀፍ ነገ በሆለታ ከተማ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በደራሲ ታሪኩ ካሣሁን የተፃፈውና በፍቅር በማህበራዊና በመሰል ጉዳዮች ላይ 12 አጫጭር ታሪኮችን ያካተተው ‹‹ከእስከ›› መፅሐፍ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ሆለታ በሚገኘው ኒያላ ሆቴል ይመረቃል፡፡በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ወጣትና አንጋፋ ደራሲያንና ገጣሚያን ከአዲስ አበባ የተጋበዙ ሲሆን ስራዎቸውን እንደሚያቀርቡ የምርቃ ስነ-ስርዓት አስተባባሪው አቶ ጌታቸው አለሙ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ከእስከ፣ የተከፈለበት፣ ስድስተኛ፣ ከዚያም ከዚህም እና ሌሎችንም አጫጭር ታሪኮች ያካተተው መፅሀፉ በ120 ገፅ ተቀንብቦ በ45 ብር ለገበያ መቅረቡን አቶ ጌታቸው
ዓለሙ ጨምረው ገልፀዋል፡፡  

Read 836 times