Monday, 03 April 2017 00:00

“ሴቶች ይችላሉ”ማህበር አንጋፋ ሴቶችን ሸለመ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   “ሴቶች ይችላሉ” (women can do it) ማህበር የዘንድሮውን “የሴቶች ቀን” ምክንያት በማድረግ “ጣዝሙቶቻችንን እናመስግን” የተሰኘ የኪነጥበብና የሽልማት ፕሮግራም ከ ትላንት በስቲያ አካሂዷል።የኪነጥበብ ዝግጅቶቹ በወንዶች የተከወኑ ሲሆን ግጥም፣ የክራር ድርደራ፣ “ትችያለሽ” የተሰኘ ቴአትርና ስታንዳፕ ኮሜዲ ለታዳሚው ቀርቧል፡፡
በዚህ ፕሮግራም ላይ 20 ያህል አንጋፋ ሴቶች የተሸለሙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ኮሚሽነር የአለም ፀሐይ ካሳ፣ የ91 ዓመቷ የእድሜ ባለፀጋና የመጀመሪያዋ የፋሺን ዲዛይነር ወይዘሮ ፅዮን አምዶም፣ የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ ዕሌኒ መኩሪያና በኢትዮ ቴሌኮም የሴቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ የአለም ስዩም ይገኙበታል። እናቷ እውቅ ሰዓሊ የነበሩትና በአሁኑ ሰዓት የቴአትር መምህርና በ”የማለዳ ኮከቦች” የተሰጥኦ ውድድር ላይ በዳኝነት የምትሰራው የእናቷ ውጤት በመሆኗ፣ የዕለቱ ብቸኛ ወጣት ተሸላሚ መሆኗንም ማህበሩ ገልጿል፡፡


Read 808 times