Saturday, 01 April 2017 14:51

የአውሮፓ ህብረት በጋዳፊ ልጅ ላይ የጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ተወሰነ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የአውሮፓ ህብረት በቀድሞው የሊቢያ ፕሬዚዳንት ሙአመር ጋዳፊ ሴት ልጅ አይሻ ጋዳፊ ላይ ጥሎት የቆየውን ማዕቀብ እንዲያነሳ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰጠቱን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘገበ፡፡
ህብረቱ እ.ኤ.አ በ2011 አይሻን ጨምሮ በተወሰኑ ሊቢያውያን ላይ የጉዞ ማዕቀብና ሃብታቸው እንዳይንቀሳቀስ የሚያስችል ትዕዛዝ ማስተላለፉን ያስታወሰው ዘገባው፤ ከ3 አመታት በኋላ የሌሎቹ ማዕቀብ ሲነሳ የአይሻ በዚያው መቀጠሉንና ማዕቀቡ ይነሳልኝ ስትል ያቀረበቺው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ገልጧል፡፡
አይሻ በቅርቡ በፍርድ ቤት በመሰረተቺው ክስ፤ አባቷ ከሞቱና አገዛዛቸው ካከተመ በኋላ በእሷ ላይ የተጣለው ማዕቀብ አለመነሳቱ አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ የተከራከረች ሲሆን ፍርድ ቤቱም አቤቱታዋ አግባብነት ያለው መሆኑን በመጥቀስ ማዕቀቡ እንዲነሳላት ወስኗል፡፡ የአውሮፓ ህብረት መንግስታትም ለፍርድ ቤት ክርክር የወጣውን ወጪ እንዲሸፍኑ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
አይሻ እና ሌሎች የተወሰኑ የጋዳፊ ቤተሰቦች እ.ኤ.አ ከ2013 አንስቶ በኦማን በጥገኝነት እየኖሩ እንደሚገኙም ዘገባው አስታውሷል፡፡

Read 1701 times