Monday, 10 April 2017 10:29

ኢዴፓ በድርድሩ እቀጥላለሁ አለ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

  የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በስራ አስፈፃሚው ሰፊ ክርክርና ውይይት ካደረገ በኋላ “ድርደር ያለ አደራዳሪ አይሆንም” የሚለውን አቋሙንሳይለቅ በድርድሩ ሂደት እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡ ፓርቲው ትናንት ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ በሰጠው መግለጫ፤ ድርድሩ በገለልተኛ አካል እንዲካሄድ የቀረበው የተቃዋሚዎች ጥያቄ ምክንያታዊና ትክክለኛ ቢሆንም በሰጥቶ መቀበል መርህ፣ በድርድሩ እቀጥላለሁ
ብሏል፡፡ የድርደሩ ሂደት ገና ከጅምሩ ለመዳከሙ ኢህአዴግ ግትር አቋም መያዙና ተቃዋሚዎች ያለ አሳማኝ ምክንያትከድርድሩ እየወጡ መሆናቸው ነው ብሏል - ፓርቲው፡፡ ፓርቲው አደራዳሪ መኖር አለበት የሚለውን አቋሙን ሳይለቅ በድርድሩ ለመቀጠል የወሰነው ሀገሪቱ
ለምትገኝበት ሁኔታ ወሳኙ የመፍትሄ መንገድ ድርድርና ውይይት ብቻ መሆኑን አበክሮ ስለሚያምን መሆኑን አስታውቋል፡፡

Read 3412 times